እንደዚህ ያለ ሌላ ዜና የለም። ሌላ ኃይማኖቶች በሙሉ የተገላቢጦሽ ነው የሚሉት። ሌሎች ኃይማኖቶች እኛ እንድንፈልግ ይነግሩናል። እንደ ዘኪዎስ ዛፍ ላይ እንድንወጣ፣ ወደ ሰማያዊው የመጠጋት ተስፋችንን በእራሳችን ጥረት ላይ እንደገፍ ዘንድ እንመክራለን። ያለውን ክፍተት እራሳችን እንድንሞላ ይነገረናል። ስለዚህ ደኅንነታችሁን ከፈለጋችሁ ፈልጉት ይሉናል።
በአንድ በኩል ዓለም እንደዚህ ናት ፈላጊ በሞላባት ምድር ላይ ነው የምንኖረው። በአንድም በሌላ መልኩ ዛፍ የምንወጣ ፣ ጥቅምን የተለየ እይታን እና የግል ሰላምን ለማግኘት አቅጣጫችንን የምንቀያይር ነን። ከዛ ግን ኢየሱስ መጣ።
ኢየሱስ መጥቶ “ፈጥነህ ውረድ” (ሉቃስ 19፡5) ፈጥነህ ውረድ እስኪለን ድረስ በፍለጋችን ውስጥ ጠፍተን ነበርን። መፈለጋችሁን አቁሙ። እራሳችሁን ለማዳን ጥረት ማድረጋችሁን አቁሙ። የጠፋውን ልፈልግና ላድን መጥቻለሁና።
የዚያን ጊዜ የእራሳችን ጥረት ፀጥ ይላል። ፍለጋችን ሁሉ ፤ መለኮትን በእራሳችን ጥረት ለመጠጋት መሞከራችን ሁሉ መለኮት ከእኛ እንደ አንዱ በመሆን ወደ እኛ እንደተጠጋ ስንረዳ ፀጥ ይላል። እግዚአብሔርን ለማግኘት በዳከርንባቸው ያነሱ ሥራዎች መሃል እግዚአብሔር ሊያገኘን መጣ። ያ ልንሞላው ያልቻልነው ገደል እርሱ የተሸከመው ሸክም ሆነ።
ፍለጋችን ሁሉ ፤ መለኮትን በእራሳችን ጥረት ለመጠጋት መሞከራችን ሁሉ መለኮት ከእኛ እንደ አንዱ በመሆን ወደ እኛ እንደተጠጋ ስንረዳ ፀጥ ይላል።
የእግዚአብሔር ፍርድ በትክክልም ይገባን የነበርን የጠፉ ኃጢያተኞች ነበርን። ኢየሱስ ግን ይህንን ፍርድ ሰለ እኛ ሊወስድ መጣ። በእኛ ምትክ በመስቀል ላይ ተሰቃየ ሞተም ደግመም ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን በሕይወት ተነሳ። ሁሉን ወደሚገዛበት ወደ አባቱ ቀኝም አረገ። ኢየሱስ ፈልገን ብናምነውም ደግሞ አድኖናል። ይህን ታምናላችሁ? የዚህ ድኅነት ድንቅ ይሰማችኋል?
ኢየሱስ ሆይ የምታድነው እኛ ሳንሆን አንተ ነህ። ስለዚህ እረፍት እምነት የሌለውን የሥራችንን ወጀብ ስለገሰፅህ እናመሰግናለን። የነፍሳችንን ትግል ስላስቆምህ እናመሰግንሃለን። በጸጋህ ክብር ዘወትር እየማረከን “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” የሚለውን የወንጌልን አጠቃላይ ሀሳብ ለሌሎች ማስተጋባት እንድችል አድርግ።
Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe