Monday, 15 July 2024

ምስጋና ለመስጠት 32 ምክንያቶች

Posted On %PM, %10 %667 %2016 %18:%Dec Written by

እንግሊዛዊው ፓስተር እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ማቲው ሄነሪ (1662-1714) ከመሞቱ 2 ዓመት በፊት ስለ ጸሎት መጽሐፍ ጽፎ ነበር። ለጸሎት የሚሆን መንገድ የሚለው ይህ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስን የማሰላሰል እና መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ የጸሎት ሕይወት ውጤት ነው። ይህ መጽሐፍ ክርስቲያኖችን በአድናቆት ፣ በመናዘዝ ፣ በልመና ፣ በምስጋና ፣ በምልጃ ደግሞም በማጠቃለያ ጸሎት እንዴት መጸለይ እንደሚችሉ የሚያስረዳ ረቂቅ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን በቂነት በመስጠት ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀን እንሆን ዘንድ ያደርገናል በሚል ተስፋ በእያንዳንዱ ርዕስ ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ጸሎት ያቀርባል። ሄነሪ እግዚአብሔርን መልሰን ለማናገር በዋነኘነት የምንጠቀምበት የንግግራችን መዝገበ ቃል የእራሱ የእግዚአብሔር ቃል እንዲሆን ክርስቲያኖችን ያበረታታናል።

ምስጋና መስጠት በሚለው ርዕስ ስር እግዚአብሔርን ለመልካምነቱ ሁሉ የተለየ ምስጋና ልንሰጥ እንደሚገባ ሄነሪ ያብራራል። በመቀጠልም ሰው ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋናን ሊያቀርብ የተገባባቸውን ምክንያቶች ይዘረዝራል። ህይወታችንን ደግፎ ይዞታል። በሕይወት ለመኖራችን የሚየስፈልጉ ነገሮችን በሙሉ ያሟላል። ፀሀይ ብርሃኗን ትሰጣለች። ዝናብ ይዘንባል። ወቅቶች ከአንዱ ወደ አንዱ ይፈራረቃሉ። ትውልድ ይቀጥላል። ነገር ግን ክርስቲያኖች ምስጋና ሊሰጡባቸው የሚገቡ አንዳነድ ነገሮች አሉ። ሄነሪ ለምስጋና ምክንያት የሚሆኑ 32 ነገሮችን ይዘረዝራል። ይህ ዝርዝር በጎ ለሆነው አምላካችን የምስጋና ጸሎት እንድናቀርብ በቂ ምክንያት ይሰጠናል።

1. ሰው ጠፍቶ እና የማይረባ ሆኑ ሳለ እግዚአብሔር ተቤዠው ፤ አዳነውም። 

እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን። ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።” (ቲቶ 3፡3-6)

2. ስለሰው ልጆች መቤዠት የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አላማ እና ምክር። 

በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።” (ኤፌሶን 1፡3-4)

3. ቤዛ ስለሆነልን።

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐንስ 3፡16)

4. ሰውን እንደሚያድን በመጀመሪያው ስለሰጠው ተስፋ።

በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።” (ዘፍጥረት 3፡15)

5. ለብሉይ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያን ስለሰጠው ሞገስ።

“በባሪያው በሙሴ ከሰጠው ከመልካም ተስፋ ሁሉ አንድ ቃል አልወደቀም።” (1 ነገሥት 8፡56)

6. የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሆኖ ወደ ዓለም መምጣቱ። 

“ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።” (ዮሐንስ 1፡14)

7. የማዳኑን ሥራ ልጁ እንዲሰራ እግዚአብሔር አብ መፍቀዱ።

“አብ ለሰጠው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣንን ሰጠው።” (ዮሐንስ 17፡2) 

8. ስለ ክርስቶስ ፍጹምነት።

“ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ!” (ማቴዎስ 27፡54)

9. ለኃጢያተኞች ክርስቶስ ማጽናኛ ስለመሆኑ።

“ጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና።” (ማቴዎስ 9፡13)

10. የክርስቶስ ቤዛነት ሙሉ በሙሉ አጥጋቢ ስለመሆኑ።

“ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን።” (ገላትያ 3፡13)

11. በሦስተኛው ቀን ስለመነሳቱ።

“ስለዚህ ነገር ሙታንንም ሕያዋንንም ይገዛ ዘንድ ክርስቶስ ሞቶአልና ሕያውም ሆኖአልና።” (ሮሜ 14፡9)

12. ወደ ሰማይ ስላረገ እና በአብ ቀኝ ስለተቀመጠ።

“በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን።” (ዕብራውያን 8፡1)

13. ስለኛ ስለመማለዱ። 

“ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” (1 ዮሐንስ 2፡1)

14. ስለ ከርስቶስ ገዢነት እና ሉአላዊነቱ።

“የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።” (ራዕይ 19፡16)

15. ስለ ክርስቶስ ዳግም መምጣት። 

“አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።” (ራዕይ 22፡20)

16. ስለ መንፈስ ቅዱስ።

“እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።” (ኤፌሶን 1፡13-14)

17. ስለ ጸጋው ኪዳን።

እግዚአብሔር በክርስቶስ “የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አድርጓል” (ኢሳይያስ 55፡3)

18. ስለ መጽሐፍ ቅዱስ 

“መጽሐፍት ሰለ ክርስቶስ ይመሰክራሉ” (ዮሐንስ 5፡39)

19. ስለ ሰንበት እና ስለ ቤተክርስቲያን አገልግሎት

“እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።” (ኤፌሶን 4፡11-13)

20. በዓለም አቀፍ ደረጃ ቤተክርስቲያን እያደገች ስላለች።

“እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።” (የሐዋርያት ሥራ 19፡20)

21. ስለ ቤተክርስቲያን መጠበቅ 

ቤተክርስቲያንን “የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” (ማቴዎስ 16፡18) 

22. ስለ ሰማዕቶች እና መስካሪዎች

“እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።” (ዕብራውያን 12፡1)

23. ስለቅዱሳን አንድነት እና የአማኞች ሕብረት

“አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።” (1 ቆሮንቶስ 10፡17)

24. ስለዘላለም ሕይወት ተስፋ 

“በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ።” (ቲቶ 1፡2)

25. ሕሊናችንን ለማንጻት መንፈስ ቅዱስ ስለሚሠራው ሥራ።

“እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ።” (ሮሜ 2፡15)

26. በእግዚአብሔር አማካኝነት በእኛ ላይ ስለሆነ መዳን።

“እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።”

27. ስለ ኃጢያታችን መሰረዝ እና ስለ ሕሊናችን ሰላም 

“ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ ፥ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፥ ደዌሽንም ሁሉ የሚፈውስ፥ ሕይወትሽን ከጥፋት የሚያድናት፥ በምሕረቱና በቸርነቱ የሚከልልሽ፥ ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጕልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።” (መዝሙር 103፡2-5)

28. ስለ ቀደሰን እና ጠብቆ ስላኖረን ሰማያዊ ጸጋ።

“በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ ነፍሴን በኃይልህ በብዙ አጸናሃት።” (መዝሙር 138፡ 3)

29. ከእግዚአብሔር ጋር በቤተ ክርስቲያን በኩል ስላለ ጣፋጭ አንድነት። 

“ከቤትህ ጠል ይጠጣሉ፥ ከተድላም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ። የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።” (መዝሙር 36፡8-9)

30. ስለጸሎት መልስ

“ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።”

31. በመከራ ጊዜ ስላለ እርዳታ 

“የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን። የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና።" (2 ቆሮንቶስ 1፡3-5)

32. ስለ እግዚአብሔር ተስፋዎች ታማኝነት።

“እግዚአብሔር ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።” (ኢያሱ 21፡45)

 

Originally Posted at The Christward Collective, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %788 %2016 %20:%Dec
Donny Friederichsen

Donny Friederichsen is pastor of Covenant Presbyterian Church (PCA) in Short Hills, New Jersey. He and his wife are the proud parents of three and are in the process of adopting a fourth. Donny is a graduate of the University of Tennessee and Reformed Theological Seminary (Orlando). You can find him on Twitter and his sermons and blog posts at www.covenantshorthills.org.

www.covenantshorthills.org

የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ

ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል! ክፍል ሁለት - የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ በቀደመው ክፍል ላይ ‘ፖርኖግራፊ’ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከ...

Ermias Kiros - avatar Ermias Kiros

ጨርሰው ያንብቡ

ሃሳባችሁን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት…

አንዳንድ ጊዜ ሃሳባችንን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት ውስጥ ልንጨምር ያስፈልገናል። ወደ ውስጥ በሰመጥን ቁጥር ክብደቱ ሊሰማን ይገባል...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.