“እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ" (ይሁዳ 20-21)።
ስለግል የፀሎት ጊዜያችሁ መለስ ብላችሁ የምታዩበት እና በመጪዎቹ ቀናት አንድ ወይንም ሁለት ነገሮችን ለማስተካከል የምታልሙበት ጊዜ አሁን ነው። በተለምዶ ለማደግ እና ረዘም ያለ መንገድን ለማቅናት የተሻለ የሚባለው አማራጭ አጠቃላይ እድሳት ሳይሆን አንድ ወይንም ሁለት የተወሰኑ ችግሮችን ለይቶ ማውጣቱ ነው።
ያጣችሁት ነገር ላይ ዓይንን እንደመጣል እምነትን የሚያደክም ነገር የለም።
እንደተረዳሁት ከሆነ ዓይኖቼን በቁሳዊ ማጣቶቼ ላይ ፣ በሌሉኝ ጥንካሬዎች እና በሌሉኝ ድክመቶች ላይ ባደረግሁ ጊዜ ያለማመን ሸክም ይከብድብኝና ሩጫዬን ከባድ ያደርግብኛል (ዕብራዊያን 12፡1)።
መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቸር አምላክ እንደሆነ ይናገራል። ብዙ ሰዎች ግን ይህንን ለማመን ይቸገራሉ። አንዳንዶች ጸጋ ምን እንደሚመስል ሲያስቡ ይገረማሉ። የእግዚአብሔርን ጽድቅና የእኛን የየዕለት አስከፊ ኃጢያት በጥልቀት ብናስብ እግዚአብሔርን “አሁንም ትወደኛለህ ወይ?” ወይንም “ለምንድን ነው እንደዚህ የታገስከኝ?” ወይንም “ስላደረግሁት ነገር ስለምን አልገደልከኝም?” ብለን ስንጠይቅ እራሳችንን ልናገኘው እንችላለን።
ሁላችንም ማን እንደሆንን ማወቅ እንፈልጋለን። እራሳችንን ፈልገን ለማግኘት እንጥራለን። ብዙዎቻችን የስብዕና ፈተናዎችን እና ሌላም ግምገማዎችን ወስደናል።
ይሁንና እነዚህ ፈተናዎች ጠቃሚዎች ሆነው ሳሉ፤ ቆም ብላችሁ ግን “እግዚአብሔር እኔ ምን እንደሆንኩ ያስባል?” “እኔ ማን እንደሆንኩ ይላል?” ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
ሁልጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደማደርገው በሰው ልጆች ታሪክ ሁሉ ውስጥ ከታተሙት መጽሐፍት ታላቅ ከሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ባለኝ አመታዊ የንባብ ጉዞዬ ዘፍጥረትን በማንበብ ላይ ነኝ ። አሁን አስራ አምስተኛ አመቴ ላይ ነኝ ። ሙሉ የጎልማሳ ሕይወቴን መጽሐፍ ቅዱስን ሳነብ እና ሳጠና ስላሳለፍኩ ወደጠለቀው ደረጃ የደረስኩ ይሰማኛል ። ምናልባት እራሴን እየካብኩ ነው ።
አንዳንድ ጊዜ ሃሳባችንን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት ውስጥ ልንጨምር ያስፈልገናል። ወደ ውስጥ በሰመጥን ቁጥር ክብደቱ ሊሰማን ይገባል። ወደ እዚህ ሰፊ ውቅያኖስ ቢልየን የአቅርቦት ገባር ወንዞች ይፈስሳሉ። እናም እግዚአብሔር እራሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሉ የማይቆጠሩ ሥራዎቹን ሰብስቦ በማይሳሳተው መገለጡ ውስጥ ያፈሳቸዋል። ይናገራል ፣ ያስረዳልም እናም ቃል ይገባል። የሚደንቀውንም ሉአላዊ አቅርቦቱን የተጠበቅን እና ነፃነት የሚሰማን ቦታ ያደርገዋል።
ከአድካሚ የስራ ቀን በኋላ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያዬ እየሔድኩ ሳለሁ በውስጤ ብዙ ሃሳብ ይመላለስ ነበር። ተስፋ የላቸውም ብዬ የምቆጥራቸው ነገሮች ሲበዙ ከፈረሰው...
ጨርሰው ያንብቡDaily Injera is a Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible each day.
The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.