ያጣችሁት ነገር ላይ ዓይንን እንደመጣል እምነትን የሚያደክም ነገር የለም።
እንደተረዳሁት ከሆነ ዓይኖቼን በቁሳዊ ማጣቶቼ ላይ ፣ በሌሉኝ ጥንካሬዎች እና በሌሉኝ ድክመቶች ላይ ባደረግሁ ጊዜ ያለማመን ሸክም ይከብድብኝና ሩጫዬን ከባድ ያደርግብኛል (ዕብራዊያን 12፡1)።
መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ቸር አምላክ እንደሆነ ይናገራል። ብዙ ሰዎች ግን ይህንን ለማመን ይቸገራሉ። አንዳንዶች ጸጋ ምን እንደሚመስል ሲያስቡ ይገረማሉ። የእግዚአብሔርን ጽድቅና የእኛን የየዕለት አስከፊ ኃጢያት በጥልቀት ብናስብ እግዚአብሔርን “አሁንም ትወደኛለህ ወይ?” ወይንም “ለምንድን ነው እንደዚህ የታገስከኝ?” ወይንም “ስላደረግሁት ነገር ስለምን አልገደልከኝም?” ብለን ስንጠይቅ እራሳችንን ልናገኘው እንችላለን።
ሁላችንም ማን እንደሆንን ማወቅ እንፈልጋለን። እራሳችንን ፈልገን ለማግኘት እንጥራለን። ብዙዎቻችን የስብዕና ፈተናዎችን እና ሌላም ግምገማዎችን ወስደናል።
ይሁንና እነዚህ ፈተናዎች ጠቃሚዎች ሆነው ሳሉ፤ ቆም ብላችሁ ግን “እግዚአብሔር እኔ ምን እንደሆንኩ ያስባል?” “እኔ ማን እንደሆንኩ ይላል?” ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
ሁልጊዜ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ እንደማደርገው በሰው ልጆች ታሪክ ሁሉ ውስጥ ከታተሙት መጽሐፍት ታላቅ ከሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ባለኝ አመታዊ የንባብ ጉዞዬ ዘፍጥረትን በማንበብ ላይ ነኝ ። አሁን አስራ አምስተኛ አመቴ ላይ ነኝ ። ሙሉ የጎልማሳ ሕይወቴን መጽሐፍ ቅዱስን ሳነብ እና ሳጠና ስላሳለፍኩ ወደጠለቀው ደረጃ የደረስኩ ይሰማኛል ። ምናልባት እራሴን እየካብኩ ነው ።
አንዳንድ ጊዜ ሃሳባችንን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት ውስጥ ልንጨምር ያስፈልገናል። ወደ ውስጥ በሰመጥን ቁጥር ክብደቱ ሊሰማን ይገባል። ወደ እዚህ ሰፊ ውቅያኖስ ቢልየን የአቅርቦት ገባር ወንዞች ይፈስሳሉ። እናም እግዚአብሔር እራሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሉ የማይቆጠሩ ሥራዎቹን ሰብስቦ በማይሳሳተው መገለጡ ውስጥ ያፈሳቸዋል። ይናገራል ፣ ያስረዳልም እናም ቃል ይገባል። የሚደንቀውንም ሉአላዊ አቅርቦቱን የተጠበቅን እና ነፃነት የሚሰማን ቦታ ያደርገዋል።
“እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን። ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም” (ሮሜ 5፡1-5)።
ወደ አንድ ሰው ቤት ወይንም የሥራ ቦታ ሄዳችሁ ያንን ሰው ቀርቦ መገኛኘት አስጨንቋችሁ ያውቃል? የምትገናኙበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ ልትነግሩት ያሰባችሁት ሁሉ ስትለማመዱት የቆያችሁት ነገር ሁሉ ከጭንቅላታችሁ ውስጥ በንኖ ጠፍቶ መናገር እንደምትችሉ ሁላ እርግጠኛ ላትሆኑ ትችላላቸሁ።
ሁላችንም ማን እንደሆንን ማወቅ እንፈልጋለን። እራሳችንን ፈልገን ለማግኘት እንጥራለን። ብዙዎቻችን የስብዕና ፈተናዎችን እና ሌላም ግምገማዎችን ወስደናል። ይ...
ጨርሰው ያንብቡDaily Injera is a Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible each day.
The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.