Tuesday, 22 October 2024

መንገዱ ከባድ ነው።እርሱ ግን ጠንካራ ነው።

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ኢየሱስም አለ “መንገዱ ከባድ ነው” (ማቴዎስ 7፡14)

በቀደሙት ዘመኖቻችን “ከባድ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ የምናውቅ ይመስለን ነበር። ከባድ ጥብቅ የሆነ ፣ ብዙ የሚጠይቅ እና አድካሚ ነው። ኢየሱስ መንገዱ ከባድ እንደሆነ ተናግሯል። እኛ ግን ከ ያዕቆብ እና ከ ዮሐንስ ጋር (በቃላችን ባንለውም ባልተገለጸ እምነት) “እንችላለን” (ማቴዎስ 20፡22) ስንል መለስን።

ነገር ግን ልክ እንደ ያዕቆብ እና ዮሐንስ ምን ውስጥ እንደገባን አላወቅንም። እንደ ጀማሪ ምልምሎች ጦርነት ምን እንደሆነ የገባን መስሎን ነበር። ጦርነት ከባድ ነው። ጦርነት ሲዖል ነው። በተለይ ደግሞ ጦርነታችሁ ከሲዖል ጋር ሲሆን።

ነገር ግን የሲዖልን ጦርነት ገብተን እስካየንበት ጊዜ ድረስ አልተረዳነውም ነበር። ሲዖል ታዲያ ተፈትቶ ስናየው የጦርነት ቀውሱ በወረቀት ላይ ከምናውቀው እጅግ የተለየ እንደሆነ ተረዳን።

ሰይጣን መልካምነትን አያውቅም። ክፉ ነው። ክፋቱን ደግሞ በትሮይ የደስታ እና ምቾት ፣ “የጥበብ” እና “ደኅንነት” በምቹ ቃላት እና ሀፍረት ፈረስ ውስጥ ይደብቀዋል። ሽምጥ ውጊያ እና ስለላ የእርሱ ነው። ሥነ ልቦናዊ ውጊያ እና ማማለል የእርሱ ነው። አካላዊ ውጊያ እና መጭበርበር የእርሱ ነው።

የሲዖል የመጀመሪያ ዓላማ

የሲዖል የመጀመሪያው አላማ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት ማጥፋት ነው። የተብራሩት ስልቶቹ እና ሰይጣናዊ አቅሞቹ የተመሠረቱት አንድ ነገር ላይ ነው እርሱም በቃሉ ላይ ያለንን እምነት በማሳነስ የቃሉን ኃይል መስበር ነው። አለም ሙሉ የተሰራችው እና የተያዘችው በቃሉ ነውና (ዮሐንስ 1፡3 ዕብራውያን 1፡3) ሲዖል ማሸነፍ ቢፈልግ መስበር ያለበት የእግዚአብሔርን ቃል ኃይል ነው።

ስለዚህ እራሳችንን እውነታውን እንዳናይ እይታችንን ለማበላሸት ዘወትር ከሚጥር ጠላት ጋር ስንዋጋ እናገኘዋለን። ስለዚህም ነው ይሄ ፍልሚያ የተለየ አንዳንዴም አሰቃቂ የሚሆነው።

ሲዖል ነገሮችን የማዛባት ጦርነት ነው የያዘው። በፈተናዎች ፣ በኩነኔ ፣ ተስፋ በማስቆረጥ ፣ በማበሳጨት ፣ በጥርጣሬ ፣ በህመም ፣ በድካም ፣ በመዛል እና ትዕቢታችንን እና ሀፍረታችንን አማላይ በማድረግ የክፉው መንፈስ ኃይላት ሚዛን እንድንስት እና ግራ እንድንጋባ አቅጣጫችንን እንድንቀይር ይተጋሉ። በእውነት ላይ ያለንን ትኩረት ማንሳት ብንችል ድፍረታችንን አጥተን እምነታችንን ልናጣ እንችላለን።


ስለዚህ እራሳችንን እውነታውን እንዳናይ እይታችንን ለማበላሸት ዘወትር ከሚጥር ጠላት ጋር ስንዋጋ እናገኘዋለን። ስለዚህም ነው ይሄ ፍልሚያ የተለየ አንዳንዴም አሰቃቂ የሚሆነው።


ሲዖል የጥርጣሬን ጦርነት አውጇል። በእዚህ መንፈሳዊ ውጊያችን ወቅት በጣም ከሚያሙ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሲዖል ወደ ግንኙነቶቻችን ዘልቆ መግባቱ ነው። የምንገበያይበትን የእምነት ገንዘብ ሊያበላሽ ይጥራል። ኃጢያት ሲበክል እና የጥርጣሬ ዘር ሲዘራ እና ሲበቅል ትዳሮች ይፈርሳሉ ፣ ቤተሰብ ይበተናል ፣ ጓደኝነቶች ይለያያሉ ፣ ቤተክርስትያኖች ይለያያሉ እናም እንቅስቃሴዎች ይቋረጣሉ። በጦርነቱ መሀል ታዲያ አቅጣጫችንን በመሳት ጠላታችን ማን እንደሆነ እንረሳ እና ከደም እና ስጋ ጋር ውጊያ እንጀምራለን።

ከዓለም ኃይሎች ሁሉ የሚበልጥ ቃሉ

ኢየሱስ ልክ ነበር መንገዱ ከባድ ነው። ከባድ ነው ብለን ካሰብነው በላይ ከባድ ነው።

ኢየሱስ ግን ስለሌላ ነገርም ልክ ነበር “የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም” (ማቴዎስ 16፡18) መንገዱ ከባድ ነው ነገር ግን መንገዱ (ዮሐንስ 14፡6) ቃል ስለሆነ (ዮሐንስ 1፡1) መንገዱ እርግጥ ነው።

እናም ይህ ቃል ሊሸነፍ በማይችል መልኩ ጠንካራ ነው።

ሁሉም የሲዖል ኃይሎች ሊያስነሱት በሚችሉት ማዛባት ፣ ሊፈጥሩ በሚችሉት አቅጣጫ ማሳት እና ሊዘሩ በሚችሉት ጥርጣሬ የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰብሩት አይችሉም። ማርቲን ሉተር ስለ ሰይጣን ያለው ልክ ነበር:- “አንድ ትንሽዬ ቃል ትጥለዋለች” የእግዚአብሔር ቃል እራሱ እግዚአብሔር ነውና (ዮሐንስ 1፡1) ያቺ ቃል ትንሽ ብቻ አይደለችም። 

እናም የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ ይህ ቃል ተገለጠ (1 ዮሐንስ 3፡9)

አቤት ግን እርስ በእርስ መጋጨቱ! የእግዚአብሔር ቃል የዲያቢሎስን ሥራ እርሱ እራሱ በመድቀቅ አፈረሰው። አዎን ከጌቴሰማኔ እስከ ቀራንዮ ድረስ የሲዖል ኃይል በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተለቀቀ እናም የእግዚአብሔር ቃል ደቀቀ። ነገር ግን ሲዖል ሊያደቅቀው እንደፈለገው ዓይነት አልደቀቀም። ሲዖል የእግዚአብሔርን ቃል ለማለዘብ ሞከረ ነገር ግን ቃሉ በመድቀቁ ጠነከረ። በደቀቀ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ሊደቀቅ የመይችል የእግዚአብሔር ቃል ሆነ። ታላቁ ቃል ኪዳን እና ፈለካዊ ፍርድ "ኢየሱስ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በእርሱ የሚያምነውን የሚያጸድቅ” (ሮሜ 3፡26) በሆነ ጊዜ ተፈጸመ።

ቃሉ ከዓለም ኃይሎች ሁሉ ልቆ የሲዖልን መዝጊያ ሰበረ።

መንገዱ ለእኛ ሊከብድ ይችላል። ነገር ግን መንገዱ ለሲዖል፣ሌላ ሲዖል ይሆንበታል።

በሲዖል ማዛበት ውስጥ ግልጽ እንዲሆንልን ቁልፉ ፣ በሲዖል አቅጣጫ መሳት ውስጥ ትኩረት እንዲሆንልን እና በሲዖል ጥርጣሬ ውስጥ መጽናታችን እና ሁሉን ቻዩ ፍቅራችን የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማ ዘንድ እረሳችንን የእግዚአብሔር ቃል በሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መክተት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ጋሻችን ነው (መዝሙር 18፡30)። ቃሉ ሰላማችን ነው (የሐዋርያት ሥራ 10፡36 ፤ ፊሊጵስዩስ 4፡7) ቃሉ ደግሞ የጦር እቃችን ነው (ኤፌሶን 6፡17)

ሲዖል አንድ ነገርን ፍለጋ ላይ እንደሆነ ልናስታውስ ያስፈልገናል እርሱም እምነታችንን ነው። ሲዖልንም ልናሸንፍበት የምንችለው በአንድ ነገር እንደሆነ ልናውቅ ያስፈልጋል እርሱም እምነታችን ነው (1 ዮሐንስ 5፡4) ኢየሱስ ሲዖልን የምንቋቋምበትን ትልቁን መንገድ በአንድ ዐረፍተ ነገር ሲናገር “በእግዚአብሔር እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ” (ዮሐንስ 14፡1) ይላል።

ስለዚህ ዛሬ:-

"በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል።" (1 ጴጥሮስ 5፡8-10)

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %AM, %27 %997 %2017 %01:%Jan
Jon Bloom

Jon Bloom serves as author, board chair, and co-founder of Desiring God. He is author of three books, Not by Sight, Things Not Seen, and Don’t Follow Your Heart. He and his wife live in the Twin Cities with their five children.

https://twitter.com/Bloom_Jon

መጽሐፍ ቅዱሳችንን ችላ ምንልባቸው ምክንያቶች

የእያንዳንዱ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ከመነበብ ብዛት ያረጀ፤ በየቦታው የተሰመረበት፤ በተለያዩ ቀለማት የተፃፉ መንፈሳዊ ሃሳቦችን የያዘ ማስታወሻ አብሮት ያለ ...

Tony Reinke - avatar Tony Reinke

ጨርሰው ያንብቡ

ብዙ ክርስቲያኖች ደስተኛ ያልሆኑት ለምንድን ነው?

ለምንድን ነው ብዙ ክርስቲያኖች ደስተኛ ያልሆኑት? ደስታ የደህንነት ስሜት ነው። “. . .  የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ...

Jim Johnston - avatar Jim Johnston

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.