Monday, 15 July 2024

አስታውሱ ፤ ይወድዳችኋል

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ" (ይሁዳ 20-21)።

በእግዚአብሔር ፍቅር እራሳችንን እንድንጠብቅ መታዘዛችን እንዴት ድንቅ ነገር ነው።

ከእግዚአብሔር ፍጽምናዎች ውስጥ ፍቅሩን ለይቶ አጽንኦት መስጠቱ ለምንድን ነው? ክርስቲያን ሰዎችን በእምነት እንዲጸኑ ሲያበረታታ ለምን ፍርዱ ላይ ወይንም ትዕግስቱ ላይ አሊያም ምህረቱ ላይ አላተኮረም? 

የይሁዳን አደራ ቸል ልንል ወይንም የአብን ፍቅር አሳንሰን ልናይ መድፈር እንኳን የለብንም። ቻርልስ ስፐርጀን እንዳለው “የእግዚአብሔር ፍቅር ሙሉ ልባችንን ላይ ሲፈስስ ፣ ጣዖቶቻችን ወዲያዉኑ ይለቅቃሉ የኃጢያትም ፍቅር በርሮ ይጠፋል”። ቅድስና አዲስ መውደድ ነው እንጂ መሸሽ ብቻ አይደለም። በፍቅሩ ብርሃን የልባችንን ጣዖታት ማስወገድ እንችል ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቅር እራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል።


“የእግዚአብሔር ፍቅር ሙሉ ልባችንን ላይ ሲፈስስ ፣ ጣዖቶቻችን ወዲያዉኑ ይለቅቃሉ የኃጢያትም ፍቅር በርሮ ይጠፋል”። ቅድስና አዲስ መውደድ ነው እንጂ መሸሽ ብቻ አይደለም። በፍቅሩ ብርሃን የልባችንን ጣዖታት ማስወገድ እንችል ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቅር እራሳችንን መጠበቅ ይኖርብናል።- ቻርልስ ስፐርጀን


“የእግዚአብሔር ፍቅር” ስንል ግን ምን ማለታችን ነው? 

የእግዚአብሔር ፍቅር ጨረር

ፍቅር የሌለን ከሆንን እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ እግዚአብሔርን ልናውቀው እንደማንችል ከ 1 ዮሐንስ 4፡8 እንማራለን። የፍቅሩ በሙላት መገለጥ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ የመጣ ነው። “እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል” (1 ዮሐንስ 3፡16)።

ኢየሱስ ክርስቶስ እና ሊፈጽምልን የቻለው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ ጣሪያ ናቸው። ኢየሱስ ሊፈጽምልን የቻለው ነገር ምንድን ነው? እርቅ:- ግንኙነታችንን ወደ ቀድሞው መለሰልን። እግዚአብሔር ቀድሞ እንኖርበት የነበረውን አለመስማማት በልጁ ሕይወት ሞት እና ትንሳኤ ከእራሱ ጋር በማስታረቅ አስወግዶታል። ኢየሱስ ወደ ዘላለማዊ የፍቅር ምንጭ ይመራናል። ጆን ኦውን ይህ ምስል ግሩም አድርጎ ያስቀምጠዋል:-

"ከጨረሩ ውጪ ለእኛ ብርሃን ባይሆንልን ነገር ግን በጨረሩ ውስጥ ምንጩ የሆነውን ፀሀይን እናያለን። መዝናኖቶች ሁሉ በምንጩ ዳር ቢሆኑ በእነርሱ ግን ወደ ፏፏቴው እናመራለን። የአብን ፍቅር በተመለከተ ኢየሱስ ብርሃናችን እና መዝናናታችን ሁሉ በእርሱ ዘንድ የሚገኝበት ጨረራችን እና ምንጫችን ሲሆን በእርሱ ግን ወደ ፏፏቴው ፣ የዘለአለም የፍቅር ፀሀይ ወደሆነው እናመራለን" (ሕብረት ከሥሉስ አምላክ ጋር ገጽ 112 )

ከንፈሮቻችን ጣዖታትን በመምጠጥ ለደረቁብን ፣ ከአናሳ ፍቅር ጥላ ስር ተደብቀን ነፍሳችን ለደረቀችብን ፣ ልባችን ከጽዋው ሙሉ ጠጥታ በማይጠፋ ብርሃን እንድትጥለቀለቅ የምንሻ ሁሉ ወደ ኢየሱስ ብቻ ነው መዞር ያለብን።

በኢየሱስ ውስጥ አብ ለእኛ ያለውን ፍቅር ልናውቅ እንችላለን። 

እዩና የእግዚአብሔርን ፍቅር ተቀበሉ

በእግዚአብሔር ፍቅር እራሳችንን መጠበቅ በእይታ ይጀምራል። መንፈስ ቅዱስን አብን በትክክል እንድናይ እንዲረዳን በመጠየቅ ይጀምራል። ማየት ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ሁኔታችን ውስጥ የአብ ልብ ስለእኛ ለመልካማችን እንደሆነ ማመን አለብን።

በልባችን ውስጥ ያሉትን ጣዖታት ለመግደል እና በእግዚአብሔር ፍቅር እራሳችንን ለመጠበቅ ልቡ ወደ እኛ ፍቅር እንጂ ነቀፋ እንዳልሆነ ማመን አለብን። የእግዚአብሔርን ልብ ደግ ፣ ርኅሩኅ እና አፍቃሪ እንደሆነ በማየት እና በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ እንደተደሰተ በማመን ይጀምራል። እንደኔ ላሉ ኃጢያተኞች እግዚአብሔር መሆን ያለበት እንዲህ እና እንዲያ ነው ከሚል ሀሳብ ይልቅ  የአብን ፍቅር እንድናይ እና እንድናምን ፤ የእግዚአብሔርን ፍቅር በልባችን ውስጥ የሚያፈስስን መንፈስ ቅዱስ (ሮሜ 5፡5) እንለምናለን።

ብዙዎቻችን ይህንን ደረጃ ስለዘለልን ፤ የእግዚአብሔርን ፍቅር ስላልተቀበልን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ደካማ ነው። በዚህም ምክንያት ልባችን እረፍት አልባ ነች። ነፍሳችን እረፍቷን ለማግኘት ያለማቋረጥ በሥራ ላይ ነች። እረፍት ቢስ የሆንነው ፍቅር እንደሆነ ማየት ስለሚያስቸግረን ነው።


ብዙዎቻችን ይህንን ደረጃ ስለዘለልን ፤ የእግዚአብሔርን ፍቅር ስላልተቀበልን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት ደካማ ነው። በዚህም ምክንያት ልባችን እረፍት አልባ ነች። ነፍሳችን እረፍቷን ለማግኘት ያለማቋረጥ በሥራ ላይ ነች። እረፍት ቢስ የሆንነው ፍቅር እንደሆነ ማየት ስለሚያስቸግረን ነው።


ጆን ኦውን እንደገና ሊረዳን በሚችል መልኩ ሲናገር “እግዚአብሔርን ፍቅር አድርገን ልናይበት የማንችለው እያንዳንዱ ስለእርሱ ያለን የእውቀት ግኝቶች ነፍሳችን በርራ እንድትጠፋ ያደርጋሉ።” ለእኛ ያለውን ፍቅር ባለማመናችን ምክንያት ለምንድን ነው ሌሎቹ ስለ እግዚአብሔር የምናገኛቸው እውቀቶች ከእሱ በርረን እንድንጠፋ የሚያደርጉን? ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሉአላዊነት እና ሥልጣን ጠላታችን ቢሆኑ ሁላችንም ከእርሱ ለመደበቅ እንሮጥ ነበር። የእርሱን ተቀባይነት ለማግኘት በመኖር እና እግዚአብሔር ተቀብሏቸው እንደሚኖሩ ልጆች መሀከል ባለ የፍትጊያ ሸክም ስር እንጨፈለቅ ነበር።

ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ሕብረት በክርስቶስ ኢየሱስ በተገኘው ይቅርታ እና ወደ እግዚአብሔር ቤተሰብ ልጆች ሆነን እንደተወለድን እንዲሁም የአብ ፍቅር የማይቀየር እንደሆነ በማመን ነው። እዚህ መጀመር ብቻ ሳይሆን እንቀጥላለን።

እራሳችንን በእግዚአብሔር ፍቅር ለመጠበቅ ጥረት እናደርጋለን።

ለእግዚአብሔር ያላችሁን ፍቅር አቀጣጥሉ 

ተግባራዊ ከሆነ ነገር ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረን ግንኙነት አብ በኢየሱስ ምናችን እንደሆነ ማመን እና ማየት እንድንችል መንፈስ ቅዱስን እንዲረዳን መጠየቅ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉት ተስፋዎች ላይ እየተመላለስን እና እጅግ ስለሚገርመው ለእግዚአብሔር ስላለብን ዕዳ በማሰላሰላችን እርሱ አስቀድሞ ወድዶናልና ልባችን በእርሱ በሐሴት ሲቀጣጠል እና ፍቅራችን በአብ ፍቅር ሲነሳሳ እናያለን።  ሲ. ኤስ. ሉዊስ “የክብር ሸክም” (The Weight of Glory) በሚለው ስብከቱ እንዳስቀመጠው፡-

እግዚአብሔርን ለማስደሰት መቻል . . . በዚህ መለኮታዊ ደስታ ውስጥ አንድ አካል መሆን . . . በእግዚአብሔር መወደድ ፣ እንዲሁ ሰዓሊ በሥራው ደስ እንደሚለው ወይንም አባት በልጁ እንጂ እንዲሁ ከሃዘኔታ ብቻ ያለመሆኑ — ሀሳባችን ሊሸከመው የማይችለው የክብር ሸክም ፣ የማይቻል ነገር ይመስላል። ነገር ግን እንዲሁ ነው።

እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ልብ የፍቅር እንደሆነ ስንመለከት ለእግዚአብሔር ያለንን የፍቅሩን እሳት እናቀጣጥላለን። በዚህ ያለን ሕይወት ውስጥ ያሉ ሁኔታዎች ምንም እንኳን ከደስታ የራቁ ቢመስል የእግዚአብሔርን ፍቅር ስናይ እና ስናምን በእግዚአብሔር ሐሴት እያደረግን በእምነት እና በደስታ መራመድ ምን ማለት እንደሆነ እንማራለን። 


እግዚአብሔርን ለማስደሰት መቻል . . . በዚህ መለኮታዊ ደስታ ውስጥ አንድ አካል መሆን . . . በእግዚአብሔር መወደድ ፣ እንዲሁ ሰዓሊ በሥራው ደስ እንደሚለው ወይንም አባት በልጁ እንጂ እንዲሁ ከሃዘኔታ ብቻ ያለመሆኑ — ሀሳባችን ሊሸከመው የማይችለው የክብር ሸክም ፣ የማይቻል ነገር ይመስላል። ነገር ግን እንዲሁ ነው።


 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %864 %2016 %22:%Dec
Joseph Tenney

Joseph Tenney is the music and arts pastor at Church at the Cross. He lives in Texas with his wife, Kimberly, and their two girls, and is a singer-songwriter in their band March of Morning.

twitter.com/josephtenney

የተስፋ ክምሮች

አጥብቃችሁ በፈለጋችሁት ጊዜ ልታገኙት የምትችሉት የተስፋ መጠን እጅግ ድንቅ ነው። ተስፋ ደግሞ በሕይወታችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ኃይል ነው። ከእግዚአብሔር የ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ

የሰው ህይወት በምድር ላይ ብዙ ሰልፍ፣ ብዙ መከራ፣ ብዙ ፈተና እንዳለበት የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። የመከራውም ሆነ የፈተናው ዓይነት ብዛቱም ሆነ ዐይነቱ ...

Eyob B Kassa - avatar Eyob B Kassa

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.