Tuesday, 22 October 2024

ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት

Posted On %AM, %10 %041 %2017 %03:%May Written by

ወደ እግዚአብሔር በቀረብንበት በዚያ ስፍራ ከመገኘቱ ጋር ደግሞ እንገናኛለን። በተዘረጉ እጆቹ ሊቀበለን ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን። መገኘቱ ሊሰማን እንደሚገባ ከተሰማን በቅድስናው ታላቅነት ልንሸፈን እንችላለን። ይህን ደግሞ ኢሳይያስ ከእግዚአብሔር ጋር ሲገናኝ ከሆነው ማየት እንችላለን። 

ኢሳይያስ 6፡1-5

“ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር። አንዱም ለአንዱ። ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር። የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት። እኔም ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ”።

ከእግዚአብሔር ጋር እንደ ኢሳይያስ ስንገናኝ 3 ነገሮች ይሆናሉ፡-

1. ሰዋዊ ማንነታችንን እናስተውላለን።
ከእግዚአብሔር መለኮትነት ጋር ሲነጻጸር እኛ ሚዛን አንደፋም። በአንደበታችን ባይሆንም በድርጊታችን ግን ከእግዚአብሔር የበለጠ እና የተሻለ እንደምናውቅ በማሰብ በእራሳችን መንገድ ነገሮችን ለማድረግ ስንጥር  ቆይተን ሊሆን ይችል ይሆናል። ነገር ግን እግዚአብሔርን ሙሉ በሙሉ ከሙሉ ቅድስናው እና ክብሩ ጋር አንዴ ስንገናኘው ሰዋዊነታችን ፍንትው ብሎ ይጋለጣል። ከእርሱ ጋር ስንነጻጸር ምንም ነን።

2. ውስጣችን ይገለጣል።
እግዚአብሔርን በመፍራት በጉልበቶቻችን መሆን በውስጣችን ያፈንነውን ስሜት ለመፍታት አንድ መንገድ ሊሆን ይችላል። ከገባንበት ቅዱስ መገኘት ይልቅ ስለእራሳችን የበለጠ ትኩረት ስንሰጥ እራሳችንን ከእውነተኛ አምልኮ እንከለክላለን። ውስጣችን መከፈቱ ጥሩ የትሕትና ስፍራ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ለትሑታን ጸጋን ይሰጣል።

3. ለማገልገል ኃይል እናገኛለን።
ኢሳይያስ ከእግዚአብሔር ጋር ከተገናኘ በኋላ ለማገልገል ኃይል ሆኖለት ነበር። በቁጥር 8 ላይ “የጌታንም ድምፅ ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አለሁ” ይላል። ስለ እግዚአብሔር መለኮትነት እና ስለ ኃጢያተኝነታችን ስንረዳ ጥፋታችንን ብቻ ሳይሆን የምንናዘዘው ጌታም እንደሆነ እንመሰክራለን ደግሞም ይህን ልንናገር እንሄዳለን! በጣም ከምናከብረው አንድ እውቅ ባለሥልጣን ሰው ጋር ፊት ለፊት ብንገናኝ እንድናደርግላቸው የሚጠይቁንን ነገር ሁሉ እናደርግላቸዋለን። ይበልጥ ደግሞ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ስንገናኘው ይህንን እናደርጋለን። “አልሄድም!” ማለት አንችልም። “እባክህን ምረጠኝ እና እሄዳለሁ!” ብለን ለማለት ግድ ይሆንብናል። 

ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘታችን ስለ እግዚአብሔር እና ስለ እራሳችን ያለንን አመለካከት ብቻ ሳይሆን የሚቀይረው ሕይወታችንንም እስከ መጨረሻው ይቀይረዋል! እግዚአብሔርን ዛሬ ለመገናኘት ተዘጋጁ።

መጽሐፍ ቅዱስን በግላችሁ ማንበብ

1. የእራሳችሁን ሳይሆን የጸሐፊውን ትርጉም ፍለጋ አንብቡ

ስናነብ ልናውቅ የምንፈልገው ጸሐፊው እንድናይ የፈለገውን እና በጽሑፉ እንድንለማመድ የሚፈልገውን ነው። ሲጽፍ የጻፈበት አላማ አለው። ያንን ምንም ሊቀይረው አይችልም። ያልተዛባ ያለፈ የታሪክ ክስተት ሆኖ ተቀምጧል።

እንዲሁ ለግላዊ (Subjective) ልምምዶች ብቻ አይደለም የምናነብበው። ገለልተኛ (Objective) እውነታዎችን ለማግኘት ነው የምናነብበው። ባነበብሁት ጊዜ ወደ አዕምሮዬ የሚመጣው ነገር በቂ አይደለም። የዐረፍተ ነገሩ ወይንም የቃሉ ወይንም የደብዳቤው መልዕክት ጸሐፊው እንድንረዳው የሚፈልገው ነገር ነው። ስለዚህ የንባብ ሁሉ የመጀመሪያ አላማ ጸሐፊው ሊል የፈለገውን ማወቅ ነው።

2. የመጽሐፍ ቅዱስን ጥልቅ ሀብት ለማውጣት ጥያቄዎችን ጠይቁ

ብዙውን ጊዜ ስናነብ ልንፈታው የሚገባ ጉዳይ ወይንም እንቆቅልሽ አልያም ልንገልጠው የሚገባ ምስጢር እስካልገጠመን ድረስ ጠለቅ አድርገን አናስብበትም። አዕምሯችንን ተግዳሮት ገጥሞት ከለዘብተኛ አንባቢነት ወደንቁ አንባቢነት እስካልተሸጋገርን ድረስ ብዙ መረዳቶችን ዘለናቸው እንሄዳለን።

እራሳችንን ጥያቄዎችን መጠየቅ ልንፈታው የሚገባንን ጉዳይ ወይንም ምስጢር የምንፈጥርበት መንገድ ነው። ይህም ማለት እራሳችንን አዘውትረን ጥያቄዎችን መጠየቅ አስተሳሰባችንን ንቁ እያደረገ ይጠብቅልናል። በምናነብበት ጊዜ አዕምሯችንን እያነቃቃ ወደ ምናነብበት ክፍሉ እውነተኛ ትርጉም ጠልቀን እንድንገባ ያደርገናል።

2.1. የቃሎችን ትርጉም ጠይቁ

ትርጉሞችን ጠይቁ። በእዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ የዚህ ቃል ትርጉም ምንድን ነው? በሉ።  አስታውሱ፤ እየጠየቅን ያለነው ጸሐፊው ያንን ቃል ሲጠቀም ምን አስቦ እንደሆነ ነው እንጂ እኛ የምናስበውን አይደለም። የዚህም ምክንያት ቃላት በተለያዩ ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ የተለያየ ትርጉም ስላላቸው ነው።

2.2. የሀረጎችን ትርጉም ጠይቁ

ሀረግ ማለት በውስጡ ግስ የሌለው ድርጊቶችን ወይንም ነገሮችን የሚገልጥ ነው። ለምሳሌ “በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ” በሚለው ዐረፍተ ነገር ውስጥ “በመንፈስ” የሚለው ድርጊቱን እንዴት እንደምንፈጽመው ያመላክታል። በሕይወታችን ውስጥ ኃጢያትን እንዴት እንደምንገድል ይነግረናል። እንደእነዚህ ያሉ ሀረጎችን በቅርበት በመከታተል ምን እያብራሩ እንዳሉ ጠይቁ::

2.3. በመፍትሔ-ሰጪ አያያዦች መሃል ያለውን ግንኙነት ጠይቁ

መፍትሔ-ሰጪ አያያዦች የባለቤት እና የግስ ስብስብ ቃላት ናቸው። እርስ በእርሳቸው እንዴት እንደሚገናኙ መጠየቅ ልንጠይቃቸው ከምንችላቸው ጥያቄዎች ውስጥ ዋነኛው ነው። ብዙውን ጊዜ መልሱን የያዙት ትናንሽ አያያዥ ቃላት ይሆናሉ (ለምሳሌ እንደ፡- ነገር ግን ፣ እና ፣ ስለዚህ ፣ ምክንያቱም ፣ ከሆነ. . . ወዘተ ያሉ)። አንዳንድ ጊዜ ሙሉ የሥነ መለኮት አስተምህሮ ልዩነቶች በእነዚህ ቃላት ላይ ተንጠልጥለው እናገኛቸዋለን።

2.4. አውዳዊ ፍቺው የቃላትን እና ሀረጎችን ትርጉም እንዴት ሊፈታ እንደሚችል ጠይቁ

የቃላቱን ትርጉም እስካላወቃችሁ ድረስ መፍትሔ-ሰጪ አያያዦች ምን እንደሆኑ በትክክል ልታውቁ አትችሉም። መፍትሔ-ሰጪ አያያዦቹ የትኛዎቹ እንደሆኑ እስካላወቃችሁ ድረስ ደግሞ የቃላቱን ትርጉም ልታውቁ አትችሉም። ክብ ነገር ነው። ነገር ግን ተስፋ አስቆራጭ ክብ አይደለም። ቃላት ውስን የሆነ የጋራ ፍቺ አገባብ ነው ያላቸው። ብዙውን ጊዜ የተሳሳቱ የቃላት ፍቺ ግምቶቻችን በዐረፍተ ነገሩ ወይም በአንቀጹ መጨረሻ ላይ ይታረማሉ። ቃላት በእራሳቸው ብዙ የሆነ ትርጉም ቢኖራቸውም ይዘታቸው እና በዙሪያቸው ካሉ መፍትሔ-ሰጪ አያያዦች  ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ግን ደራሲው እንዲኖራቸው የፈለገውን ትርጉም ያብራራሉ።

2.5. ከሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ስላላቸው ግንኙነት ጠይቁ

በምናነብበው ክፍል ውስጥ እያየነው ያለው ፍቺ ከሌሎች ክፍሎች ጋር እንዴት መጣጣም እንደሚችል መጠየቅ አለብን። በሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ስፍራዎች ላይ ማመሳከሪያዎች አሉ? ተቃራኒ ወይንም የሚጋጩ የሚመስሉስ ክፍሎች አሉ? በሁለት ጥቅሶች ወይንም ክፍሎች መሀል ውጥረት ሲፈጠርብኝ መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በእርሱ ይጋጫል ብዬ አልደመድምም። ነገር ግን ማየት ያለብኝን ስላላየሁ ነው ብዬ ነው የማስበው። የገጠመኝን የሀሳቦች አለመግባባት ለመፍታት የሚሆነኝን ያህል ካላየሁ የበለጠ ጥያቄዎችን መጠየቅ ምናልባት የተሻለ እንዳይ ሊረዱኝ ይችላሉ። መጀመሪያ ሲገጥሙን የማይመስሉ ነገር ግን ክፍሎቹ ከእውነታው ጋር እንዴት ተጣብቀው እንደሚቆሙ መጠየቅ ስለእግዚአብሔር ያለንን እውቀት ጥልቅ ከሚያደርጉት ጥቂት ነገሮች ውስጥ አንደኛው ነው። 

2.6. ስለ ትግበራ ጠይቁ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አላማቸው “እንድናውቅ” ብቻ ሳይሆን “እንድንሆን” ደግሞም “እንድናደርገው” ጭምር ነው። ስለዚህ መተግበርን በተመለከተ ጥያቄዎችን መጠየቅ የዘወትር ልምዳችን ሊሆን ይገባል። ለእኛ ፣ ለቤተክርስትያን እና ግንኙነቶቻችን እንዲሁም ለዓለም የመተግበር ሥራ አላበቃም። አንድን ክፍል በብዙ ሚሊየን መንገዱ ልንተገብረው እንችላለን። ሥራችን እያንዳንዱን አተገባበር ማወቅ ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ትርጉም በሕይወታችን ላይ ወደ መተግበር ማደግ ነው።

2.7. ስለ ልባችሁ ትክክለኛ ምላሽ ጠይቁ

መፅሐፍ ቅዱስ የማንበባችን ዋነኛው አላማ በአዕምሯችን ብቻ ሳይሆን በልባችንም ምላሽን መስጠት ነው። እያንዳንዱ የሰው ልጅ የስሜት ገለጻዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉምም ሊቀርቡ የሚችሉ ምላሾች ናቸው። እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን የሰጠን አዕምሯችንን ብቻ ለማሳወቅ ያህል ሳይሆን ልባችንንም ለመቀየር ነው። በትክክል በመረዳት ብቻ ለእግዚአብሔር ቃል ክብር አናመጣም፤ በትክክል በመኖርም ጭምር እንጂ።

3. በእያንዳንዱ ገጽ እግዚአብሔር እንዲረዳችሁ ጸልዩ ጠይቁም

እግዚአብሔር ሆይ እባክህን ልባችንን ወደ ቃልህ አዘንብል። ለቃልህ መሻትን ስጠን። በውስጡ ያሉትን ድንቆች እንድናይ ዓይናችንን ክፈት። ፍቃዳችንን አስገዝተህ የእሺታን መንፈስ ስጠን። ልባችንን አንተን በመግለጥ እና ለሕይወታችን ባለህ መንገድ አርካ።

 

Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %11 %837 %2017 %22:%May
Michelle Zombos

Born in Auckland, New Zealand to migrant parents from Western Samoa and Australia/Greece, Michelle declared at the age of six that one day she would be a “missionary” to Ethiopia. After giving her life to Jesus as a 19-year-old mother and wife, she started to serve in ministry in South Auckland’s urban community. After having her five children and graduating from Bible College, she eventually came to Ethiopia with her family where she has served a local Ethiopian Evangelical Mekane Yesus Church in Debre Zeit and Addis Ababa. She is passionate about the word of God and sharing it with those who long to connect with their Creator.

aheartforethiopia.blogspot.com/

ከታላቁ የወንጌል ሰባኪ ዶ/ር ቢሊ ግራሃም (1918-2018) ሕ…

ታዋቂው አሜሪካዊ የወንጌል ሰባኪ ዊልያም ፍራንክሊን ግራሃም ወይም በአጭሩ ቢሊ ግራሃም በ99 አመታቸው ዜና እረፍታቸው በትላንትናው ዕለት (የካቲት 14) ማለዳ...

Naol Befkadu - avatar Naol Befkadu

ጨርሰው ያንብቡ

መንገዱ ከባድ ነው።እርሱ ግን ጠንካራ ነው።

ኢየሱስም አለ “መንገዱ ከባድ ነው” (ማቴዎስ 7፡14) በቀደሙት ዘመኖቻችን “ከባድ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ የምናውቅ ይመስለን ነበር። ከባድ ጥብቅ የሆነ...

Jon Bloom - avatar Jon Bloom

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.