Friday, 29 March 2024

የተስፋ ክምሮች

Posted On %AM, %16 %041 %2017 %03:%May Written by

አጥብቃችሁ በፈለጋችሁት ጊዜ ልታገኙት የምትችሉት የተስፋ መጠን እጅግ ድንቅ ነው። ተስፋ ደግሞ በሕይወታችን እጅግ አስፈላጊ የሆነ ኃይል ነው። ከእግዚአብሔር የመጨረሻ አሸናፊነት ወደ እኛ የሚፈስስ የደስታ ወንዝ ነው። "የእግዚአብሔር ደስታ ደግሞ ኃይላችን ነው" (ነህምያ 8፡10)። አይደለም በእግዚአብሔር ነገር ልንለመልም ይቅርና ያለተስፋ መኖር አንችልም።

ምንአልባት ተስፋን አሁን እየፈለግን ካለው የበለጠ ብዙ እጅ አጥብቀን ልንፈልገው ያስፈልገናል። በልቤ ከሁሉ የሚበልጥ አንድ ተስፋ አለ። እርሱም የእግዚአብሔር የማዳን አላማ በዓለም ላይ እያየለ እንዳለ እና አንድ ቀን በፍጥረት ሁሉ ላይ ገዢ እንደሚሆን ነው።

ታዲያ ይህንን ተስፋ ከቀድሞው ይልቅ እንዴት አጥብቀን መፈለግ እንችላለን? በመጀመሪያ ለብቻችን ልናደርገው አንችልም። አብረውን ካሉት ሌሎች ማበረታቻ ውጪ እንሰጥማለን። እግዚአብሔር ለአንዱ የተስፋ ራዕይ በመስጠት ሌላውን ከከፋ ሀዘን ይጠብቃል። ሁል ጊዜ በቀጥታ አይመጣም። በእናንተ ውስጥ ያለ የእግዚአብሔር ሥራ መበረታታት እኔን ይታደገኛል። በእኔ ወስጥ ያለ የሥራው መበረታታት ደግሞ እናንተን ይታደጋችኋል።

በመቀጠልም ሆን ብለን በታቀደ ሥነ-ሥርዓት ልናደርገው ያስፈልጋል። ለእድል ወይንም ለአጋጣሚ ልንተወው የምንችለው ነገር አይደለም። አካላዊ ጥንካሬን እንደምንንከባከበው ሁሉ ስሜታዊ ጥንካሬአችንንም እየመገብን ልንንከባከበው እንችላለን። ጠንካራ ለመሆን እራሳችንን ካሳመንን ያንን ማድረግ እንችላለን። ብዙዎቻችን ተስፋችንን ለአጋጣሚዎች እንተውና ለምን ተስፋ እንደቆረጥን ግር ይለናል። 

ሃሳቤ ይህ ነው:- በወር ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ እየተገናኛችሁ በእግዚአብሔር ድል አድራጊነት ላይ ያለችሁን የተስፋ እሳት በጋራ ልታቀጣጥሉ የምትችሉትን ሰዎች ፈልጉ። ከሦስት አይነሱ። አስራ ሁለት ድረስ ሊሆን ይችላል። በየሁለት ሳምንቱ ወይንም ጊዜ ካላችሁ በየሳምንቱ ለአንድ ሰዓት ያህል ለቁርስ ወይንም ለምሳ ተገናኙ።

የተስፋ ክምሮች ብለን እንጥራው። አስታውሱ ትጋት ያለው ፍለጋን ይጠይቃል። ተስፋን የማናገኝበት አንደኛው ምክንያት ወደ ስራ በጠዋት ተነስተን በምንሄድበት ስነ ሥርዓት ስለማንፈልገው ነው። ይህ ግን ሥራ ቦታ ከመሄድ በላይ አስፈላጊ ነው።

በተስፋ ክምሮች ውስጥ እንዲህ ቢሆን ብዬ እመክራለሁ:- በእያንዳንዱ መገናኘታችሁ ላይ ለሦስት ሰዎች ለሚቀጥለው መገናኘት የሚሆን ኃላፊነት ይሰጣቸው። አንደኛው ባለማመን እና በክፉው እንዲሁም በህመም ኃይል ላይ የእግዚአብሄርን ድል አድራጊነት ተስፋ የሚያቀጣጥልን የመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ክፍል ይዞ ይምጣ። ያ ሰው ክፍሉን አንብቦ ለምን ተስፋን እንደሚሰጥ ከ 10 እስከ 15 ደቂቃዎች ያስረዳ። ሌሎች ሃሳባቸውን ያካፍሉ።

ሁለተኛው ሰው ከግለ-ሕይወት ታሪክ መጽሐፎች ወይንም ከታሪክ መጽሐፍት ውስጥ እግዚአብሔርን መንግስቱን ለማስፋት ያለውን ታማኝነት እና ኃይል የሚገልጹ ታሪኮችን ይዞ ይምጣ። ታሪኩን ሊተርከው ወይንም ሊያነብላችሁ ይችላል። ሌሎች ደግሞ ሃሳባቸውን ሊያካፍሉ ይችላሉ። ይሄንንም ከ 5 እስከ 10 ደቂቃ አድርጉ።

ሦስተኛው ሰው ደግሞ እግዚአብሔር በወቅታዊው ዓለማችን ላይ ያለውን የድል መንሳት ጉዞ የሚያወሳ ክስተትን የሚያስረዳ መግለጫ ያቅርብ። 

በመጨረሻም በመጽሐፍ ቅዱሱ ፣ ግለ-ታሪክ ማስታወሻው እና ወቀታዊ ክስተቶች ላይ ተመርኩዘን የእግዚአብሔር አላማ እንዲጸና ፣ የድል መንሳቱ ተስፋ እንዲሰማን ፣ የትንሿ ሕይወታችን የግል ችግሮች በዚህ ዓለም ላይ በድንቅ እየሰራ ባለው በተስፋ አምላክ እንዲዋጡ የፀሎት ጊዜ ደግሞ ይኖራል። 

በእያንዳንዱ መገናኘታችሁ ላይ ይህ ኃላፊነት ለተለያዩ ሦስት ሰዎች ይሰጣል።

ይሄ በእርግጥ ሰዎች ወጥተው የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎችን ፣ የድል ግለ-ታሪኮችን እና በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ነባራዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያሳድዱ እና እንዲፈልጉ ይጠይቃል። ይሁን እንጂ ልናደርግ የሚገባን ይሄው ነው። 

ነገር ግን ይህንን ከሥራችን ጋር አንድ ላይ አናደርገውም። ለመብላችን የሚሆንን እንጀራ ፣ ዞሮ መግቢያ ቤት እና መንቀሳቀሻ መኪናን ለማሟላት ስንል ተነስተን በትጋት ስንሰራ እንውላለን። ነገር ግን ተስፋ ከእነዚህ ሁሉ አይበልጥምን? ለሥራችን የምንተጋውን ያህል ታዲያ ለምን ተስፋን ለመያዝ አንተጋም?


ነገር ግን ይህንን ከሥራችን ጋር አንድ ላይ አናደርገውም። ለመብላችን የሚሆንን እንጀራ ፣ ዞሮ መግቢያ ቤት እና መንቀሳቀሻ መኪናን ለማሟላት ስንል ተነስተን በትጋት ስንሰራ እንውላለን። ነገር ግን ተስፋ ከእነዚህ ሁሉ አይበልጥምን? ለሥራችን የምንተጋውን ያህል ታዲያ ለምን ተስፋን ለመያዝ አንተጋም?


መጽሐፍ ቅዱሳችንን በአዲስ አላማ እና ትኩረት እናነብ ነበር። የእግዚአብሔርን ዱካ ፍለጋ እግዚአብሔር የተጠቀመባቸውን ወንድ እና ሴቶች አስደናቂ የሕይወት ጉዞ አቅጣጫ ይዘን ግለ-ታሪካቸውን አንጠፍጥፈን እናነብ ነበር። በእኛም ዘመን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ የሚመዘግቡ በጣም ጥሩ የሚባሉትን መጽሔቶች እና መጽሐፎች እናሳድድ ነበር።

እንዴት አይነት አስደሳች ፍለጋ ይሆንልን ነበር። ይህም ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ለመበረታታት ደግሞም ለመንግስቱ ጥቅም ነው።

የተስፋ ክምሮች! ሸክም መስሎ ቢሰማችሁ አትሞክሩት። ነገር ግን ተስፋ ከእንጀራችን እንዲሁም ከሕይወት ሳይቀር የበለጠ አስፈላጊ እንደሆነ ትርጉም ከሰጣችሁ ምናልባት ይህ ልንለማመደው የሚገባ ሥርዓት ነው።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %17 %892 %2017 %23:%May
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

ትዳር በዘላለም እይታ

ትዳራችሁ ምን ያህል ሚቆይ ይመስላችኋል? ሌላ ተጨማሪ አምስት አመት ምትቀጥሉ  ይመስላችኋል? አስርስ? ሃምሳ? ከዘላለም ጋር ሲነፃፀር ብዙም እንደማይባል ሁላች...

Francis Chan - avatar Francis Chan

ጨርሰው ያንብቡ

ክርስቶስ በጣቱ ምን ጻፈ?

ይህን የመጽሀፍ ቅዱስ ታሪክ በማነብበት ጊዜ ሁሉ እጅግ መደነቄ የማይቀር ነው። ምናልባትም በገጠራማዋ ገሊላ ይልቁንም በዚች የወይራ ዛፎች ኮረብታ በምትሆን ደብ...

Wongel Alemayehu - avatar Wongel Alemayehu

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.