Monday, 15 July 2024

ቤተ-ክርስትያን አሥራት ብታወጣ ምን ሊሆን ይችል ነበር ?

Posted On %PM, %07 %836 %2016 %22:%Dec Written by

በአሁኑ ጊዜ ያለችው ቤተ ክርስትያን መስጠት ላይ ጎበዝ አይደለችም።

ይሄ ዜና ሳይሆን በጥናት የተደገፈ እውነታ ነው።

አሥራት የሚያወጡት ሰዎች ቁጥር የጉባኤው ከ 10 እስከ 25 እጅ ብቻ ነው።  

5 በመቶው የአሜሪካ ህዝብ ብቻ ነው አሥራት የሚያወጣው። 80 በመቶው የአሜሪካ ህዝብ ደግሞ የገቢውን 2 በመቶ ብቻ ነው የሚሰጠው።  

ክርስትያኖች ደግሞ በነፍስ ወከፍ 2.5 በመቶ ብቻ ነው እየሰጡ ያሉት። “ታላቁ የድብታ ጊዜ” (the Great Depression) በሚባለው ወቅት ግን 3.3 በመቶውን ይሰጡ ነበር።  

እንደዚህ ያሉ ቁጥሮች ብዙ የጥፋተኝነት ስሜትን ሊፈጥሩ ቢችሉም ዓላማው ግን ይህ አይደለም። ዋናው ዓላማ አማኞች ቢያንስ ከሚያገኙት አሥር በመቶውን ቢሰጡ ምን ሊሆን ይችላል የሚለው ነው። ቤተ- ክርስትያን ልትጠቀመው እና ልታከፋፍለው የምትችለው ተጨማሪ 165 ቢሊየን ዶላር ይኖር ነበር። ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዋ የሚያስደንቅ ይሆን ነበር። ቤተ ክርስትያን እንደዚህ ባለ ብር ልታደርግባቸው ከምትችላቸው ነገሮች ውስጥ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው፡-

• 25 ቢሊየን ዶላር በ 5 ዓመት ውስጥ በዓለም ዙሪያ ያለ ረሀብን እና ልንከላከላቸው በሚችሉ በሽታዎች የሚመጣ ሞትን ሊያጠፋ ይችላል።

• 12 ቢሊየን ዶላር መሀይምነትን በ 5 ዓመት ውስጥ ሊያጠፋ ይችላል።

• 15 ቢሊየን ዶላር በተለይ ገቢያቸው በቀን ከ 1 ዶላር ባነሰ ገቢ የሚኖሩ 1 ቢሊየን የሚሆን ህዝብ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ ያለን የዓለምን የውኃ እና ጤና ጥበቃ ችግሮችን መፍታት ይችላል።

• 1 ቢሊየን ዶላር ሁሉንም የ ሚስዮን አገልግሎቶችን ወጪ መሸፈን ይችላል።

• እንደዚህም ሆኖ ከ 100 እስከ 110 ቢሊየን ዶላር ለተጨማሪ አገልግሎት ማስፈፋፊያ ይተርፋል።

እነዚህ በጣም የሚደንቁ ቁጥሮች ናቸው።

ለምንድን ነው ታዲያ የማንሰጠው?

ስለመስጠት ስናስብ ሁነኛው ችግር ገንዘብ አይደለም። ገንዘብ ፈጽሞ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ነገሩ የዓይኖቻችን ጉዳይ እንደሆነ ይናገራል። ኢየሱስ “ክፉ ዓይን” ይለው የነበረ ነው። ኢየሱስ እንደዚህ ብሎ ነው ያስቀመጠው፡


ስለመስጠት ስናስብ ሁነኛው ችግር ገንዘብ አይደለም።


 “መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና። የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!” (ማቴዎስ 6፡21-23)

“ክፉ ዐይን” የሚለው ሀሳብ የአይሁዶች አነጋገር ነው። “መልካም ዐይን” የሚለው ሀሳብ መልካም ፍቃድን ፤ ቅንነትን እና በሌሎች ሰዎች መበልጸግ ከልብ መደሰትን ያመለክታል። ክፉ ዐይን ግን የዚህ ተቃራኒ ነው።

“ክፉ ዐይን” ያለው ሰው ሌሎች በበለጸጉ ጊዜ ያዝናል ፤ ሌሎች በተሰቃዩ ጊዜ ሃሴትን ያደርጋል ፤ ገንዘባቸውንም ይወዳል ግን በለጋስነት ምንም ነገር አያደርግም።

ታዲያ ኢየሱስ ስለ ዐይን በተናገረ ጊዜ ፣ የሚናገረው ነገር ይገባቸው ለነበሩ የአይሁድ አድማጮቹ ነበር የተናገረው። “መልካም ዐይን” ለጋስን ሰው የሚወክል “ክፉ ዐይን” ደግሞ ንፉግ ቆንቋና ሰውን የሚወክል እንደሆነ ያውቁ ነበር።  

እውነታው መስጠት የልብ ጉዳይ እንጂ የገንዘብ ጉዳይ አለመሆኑ ነው።

ጳውሎስ ስለ መቄዶንያ አብያተ ክርስቲያናት ድንቅ ስጦታ በሚናገር ጊዜ የቆሮንቶስ አብያተ ክርስቲያናትም ልክ እንደ መቄዶንያዎች ፍቅራቸውን እንዲያስረግጡ ይገፋፋቸዋል።

ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነትና በቃል በእውቀትም በትጋትም ሁሉ ለእኛም በፍቅራችሁ እንደ ተረፋችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ትረፉ። ትእዛዝ እንደምሰጥ አልልም፥ ነገር ግን በሌሎች ትጋት በኩል የፍቅራችሁን እውነተኛነት ደግሞ ልመረምር እላለሁ”። (2 ቆሮንቶስ 8፡7-8)

ቀጥሎም አንድ ደረጃ ከፍ አድርጎት ስለፍቅር እና መስጠት ታለቁን መለኪያ ይናገራል:-

የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ አውቃችኋልና፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች ትሆኑ ዘንድ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ”። (2 ቆሮንቶስ 8፡9)

እግዚአብሔር ለ radical ሰጪዎች ሁል ጊዜም የተለየ ስፍራ አለው።  

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም”። (2 ቆሮንቶስ 9፡7)

በደስታ መስጠት ታዲያ ምን ይመስላል?

ጥቂት ሀሳቦችን እንደሚከተለው ላቀርብ እችላለሁ። ነገር የማሳስባችሁ ነገር በተራ ወይንም በተለመዱት ነገሮች ለሚረኩት እንደማይሆኑ ነው:-

• አሥራት ማውጣት ጀምሩ:-  ከላይ እንደተመለከትነው ጥናት ከሆነ አሥራታችንን በታማኝነት ብናወጣ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ልታደርግ ትችላለች። ነገር ግን ልብ ይበሉ አሥራትን ማውጣት በጀመራችሁ ጊዜ ማወቅ ያለባችሁ አሥራት የማውጣት ህግ እና አሥራትን ለማውጣት ባለ ጸጋ መካከል ልዩነት እንዳለ ነው። አሥራትን የማውጣት ሙሉ ኃይል ያለው በጸጋ ውስጥ እንጂ በፍርኃት ውስጥ አይደለም። ልናደርገው የተሰጠን ነገር እንጂ ማድረግ አለብን የምንለው ነገር አይደለም።

• አሥራትን ስለማውጣት አስተምሩ:- ይህ ቤተ ክርስቲያንን ከመሀል ሊከፋፍል ኃይል ያለው ጉዳይ ነው። ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ ሰዎች ይህን ጉዳይ የሚሸፋፍኑት አሊያም ወደማስፈራራት የሚያመሩት። ነገር ግን ጥበብ ባለው መልኩ ብናደርገው ጥሩ የሚባል መልዕክት ሊወጣው የሚችል ርዕስ ነው።

• አሥራት ማውጣትን ወደ ላቀ ደረጃ አሳድጉት:- አሥራት ማውጣት መጀመሪያ ብቻ ነው። ዓለምን ሊቀይር የሚችል ስጦታ ከሚጠበቀው እና ከተጠየቀው በላይ መስጠት ነው።  

 

Originally Posted at Relevant Magazine, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %803 %2016 %21:%Dec
Mike Holmes

I am one lady's husband and two people's dad. And I'm working on stirring up a revolution of radical giving. Other than that I'm a regular guy! For more info about that visit tithehacker.com

tithehacker.com

የተሰራችሁት ወደ እግዚአብሔር ለሚያዘነብል ሕይወት ነው

እግዚአብሔራዊ ሕይወት ወደ እግዚአብሔር በማዘንበል የሚኖር ነው። ፊታችንን ከእርሱ ሳይሆን ወደእርሱ ነው የምናዞረው። መገኘቱን ማስተዋላችንን ከጊዜ ወደ ጊዜ እ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

ጣፋጭ ወይንስ መራር ቅድስና?

ጄሪድ ዊልሰን በ አንድ መጽሐፉ ላይ ሲጽፍ “ቅድስና እንድታጉረመርሙ ካደረጋችሁ እያደረጋችሁት ያለው ነገር ልክ አይደለም” ይላል። 

Tony Reinke - avatar Tony Reinke

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.