ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሲድኒ አውስትራሊያ ነበር ያሳለፍኩት። ወቅቱ ፀደይ ስለነበር የአየሩ ሙቀት እየጨመረ ነው ፤ ቀኖቹም ረጅም እየሆኑ ነው። ፀሀይ በምትጠልቅበት ጊዜ ወጥቶ ለመንሸራሸር ደስ ይሚል አየር ነበር።
ሲድኒ ውስጥ ፀሀይ ስትጠልቅ በጣም የሚስብ እይታ ነው። እንዳስተዋልኩት ከሆነ ግን በጣም የሚያስደስት እይታ ያለው ሰማዩ ጥርት ባለባቸው ቀኖች ላይ አይደለም። ነገር ግን ሰማዩ በጨፈገገበት እና በደመና በተሞላባቸው ቀኖች ከምን ጊዜውም በላይ ያማሩ የፀሀይ ግባት እይታዎች ይኖራሉ። ደመናዎቹ ከፀሀይ የሚመጡትን የተለያዩ ቀለማት ያንፀባርቁና የእግዚአብሔርን ክብር በግልጽ ታዩታላችሁ። ሰዎች በሚያዩት ድንቅ ውበት ስለሚማረኩ ፎቶዎች እያነሱ በማሕበራዊ ድህረ ገጾች ላይ ያወጧቸዋል።
በህይወታችንም ብዙ ጊዜ ነገሮች እንዳቀድናቸው የማይሄዱባቸው ቀኖች ላይ ወይንም እንዳናረጋቸው የተገቡ ነገሮችን በማድረጋችን ምክንያት ደመናማ ቀኖችን አሊያም ደመናማ እና በወጀብ የተሞሉ ውብ ልንላቸው የማንችላቸው ወቅቶች በህይወታችን ውስጥ ልናይ እንችላለን። በወጀቡ ውስጥ የምናያቸው ደመናዎች ቀኑን ሙሉ ከሚያበራው ፤ ፈጽሞም ከማይተወን ወይንም ከማይጥለን የዓለም ብርሃን የሚጋርዱን ነገሮች ናቸው።
ፀሀይ ሁል ጊዜ በሰማይ ላይ እንዳበራች ነው። አይሮፕላን ላይ ተሳፍራችሁ የምታውቁ ከሆነ ደግሞ አንዴ ከደመና በላይ ከፍ ስትሉ የምታዩት ነገር ፀሀይ ብርሃኗን እየሰጠች እና ውብ ብርሃኗን ከደመናው በላይ እያንፀባረቀችው እንዳለ ነው። በደመና ውስጥ ሰንጥቆ ወጥቶ ልናየው ባንችልም ፀሀይ ግን ብርሃን መስጠቷን መቼም አታቋርጥም።
በህይወታችንም ብዙ ጊዜ ነገሮች እንዳቀድናቸው የማይሄዱባቸው ቀኖች ላይ ወይንም እንዳናረጋቸው የተገቡ ነገሮችን በማድረጋችን ምክንያት ደመናማ ቀኖችን አሊያም ደመናማ እና በወጀብ የተሞሉ ውብ ልንላቸው የማንችላቸው ወቅቶች በህይወታችን ውስጥ ልናይ እንችላለን። በወጀቡ ውስጥ የምናያቸው ደመናዎች ቀኑን ሙሉ ከሚያበራው ፤ ፈጽሞም ከማይተወን ወይንም ከማይጥለን የዓለም ብርሃን የሚጋርዱን ነገሮች ናቸው።
በህይወታችሁ ላይ ያንዣበበው ደመና እግዚአብሔር እንደሌለ ወይንም እንደተዋችሁ ማሰብ እንድትጀምሩ እድርጓችሁ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እሱ እንደማይተዋችሁ ቃል ገብቷል ይዋሽ ዘንድ ደግሞ አይችልም። ነገር ግን በህይወታችሁ ላይ የድንቅ ሥራውን ምስል ለማስቀመጥ እየሠራ ነው። በህይወታችሁ ውስጥ ያለውን ደመና ሰንጥቆ የወጣውን የብርሃኑን ነፀብራቅ ሰዎች ባዩ ጊዜ ይህንን ውበት በእናንተ ውስጥ ያመጣው እግዚአብሔር እንደሆነ ያውቃሉ።
ለህይወታችሁ ውበትን በመስጠት እግዚአብሔር ሰዎችን ወደ እውነተኛው ብርሃን ወደ ኢየሱስ ለመማረክ ይጠቀምባቸዋልና ወጀቦቹን አትፍሯቸው ከደመናዎቻችሁም አትደበቁ።
Translated by Joshua Terefe