Monday, 15 July 2024

ሃሳባችሁን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት ውስጥ ጨምሩ

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

አንዳንድ ጊዜ ሃሳባችንን እንደ ውቅያኖስ ሰፊ በሆነው በእግዚአብሔር ሉአላዊነት ውስጥ ልንጨምር ያስፈልገናል። ወደ ውስጥ በሰመጥን ቁጥር ክብደቱ ሊሰማን ይገባል። ወደ እዚህ ሰፊ ውቅያኖስ ቢልየን የአቅርቦት ገባር ወንዞች ይፈስሳሉ። እናም እግዚአብሔር እራሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሉ የማይቆጠሩ ሥራዎቹን ሰብስቦ በማይሳሳተው መገለጡ ውስጥ ያፈሳቸዋል። ይናገራል ፣ ያስረዳልም እናም ቃል ይገባል። የሚደንቀውንም ሉአላዊ አቅርቦቱን የተጠበቅን እና ነፃነት የሚሰማን ቦታ ያደርገዋል።

አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር እራሱ ለግዛቱ ልክ እንደሌለው ሊያስታውሰን ያስፈልጋል። በዓለም ዙሪያ እና በውስጧ ባለው ሁሉ ላይ ሉአላዊ እንደሆነ ልንሰማ ያስፈልገናል። ረዳት አጥቶ፣ የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቶ ተጨንቆ ወይንም ኪሳራ ውስጥ ወድቆ እንደማያውቅ የእርሱ የግል ማስታወሻ ያስፈልገናል። በ አይሲስ (ISIS) ላይ ፣ በአሸባሪዎች ላይ፣ በሶሪያ ፣ በሩሲያ ፣ በቻይና ፣ በህንድ ፣ በኢትዮጵያ፣ በናይጄሪያ ፣ በፈረንሳይ ፣ በማይናማር ፣ በሳውዲ አረቢያ እና በ አሜሪካ ላይ በሁሉም ሀገራት ላይ ፣ በሁሉም ህዝብ ፣ ቋንቋ እና ነገድ ላይ በሁሉም ፕሬዚዳንት ፣ ንጉስ ፣ ጠቅላይ ሚንስተር ፣ ፖለቲከኛ ላይ ትልቅ ቢሆኑ ትንሽ በሁሉ ላይ እንደሚገዛ የእራሱ ማረጋገጫ ያሻናል።

አንዳንድ ጊዜ ስለስልጣኑ ከራሱ ከእግዚአብሔር ቀጥተኛ የሆኑ ቃሎችን ልንሰማ ያስፈልገናል። የእግዚአብሔር የእራሱ ቃሎች ያስፈልጉናል። ሰውነታችንን አረጋግተው የተረጋጋን ፣ ጥበበኞች እና የተበረታታን ሊያደርጉን ኃይል ያላቸው የእግዚአብሔር የእራሱ ቃሎች ናቸው።

በሌላ በኩል የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት በሌላ ድምጾች ፈርቶ የነበረ አባቱ ግን አሁን ቤት ወደ እንደመጣ ድምጹን የሰማ ልጅ አይነት ነው። ሲረብሹት የነበሩት ድምጾች ምን እንደሆኑ ባያውቅም አሁን ግን አባቱ ስለመጣ ችግር እንደሌለበት አይነት ህፃን።

በሌላ በኩል ደግሞ ጠላት ሊያጠፋቸው እንዳሉ በጦር ሜዳው ፊት እንደ ተሰለፉ ወታደሮች አይነት ነው ስሜቱ። ግን ሊጎዱ የማይችሉ ሺህ ታንኮች ለእነእርሱ እርዳታ እንደመጡ ድምፅ ሰሙ።  ትንሽ ብቻ ነው የቀራቸው ሊደርሱላችሁ ተባሉ። ትድናላችሁ ጠላቶቻችሁም አይቆሙም።

ስለእግዚአብሔር ኃይል ያሉን እንደነገሩ የሆኑ መረዳቶች እግዚአብሔር እራሱ ሉአላዊነቱ እንዴት ኃያል እንደሆነ ፣ ኃይሉ እንዴት በሁሉም ቦታ እንደሆነ ፣ ሥልጣኑ በዓለም ሁሉ እንደሆነ ፣ ሉአላዊነቱ የማያልቅ እንደሆነ ዘመናችንም በእጁ እንዳለ በግልጽ ከሚነግረን ጋር ተመሳሳይ ውጤት የላቸውም።

ስለዚህ እንስማ። መጽሐፍ ቅዱስን እንደ እግዚአብሔር ድምጽ እንቀበለው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለእግዚአብሔር የሚናገረውን እግዚአብሔር ስለ እግዚአብሔር የሚናገረው ነው ብለን እንውሰድ። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥም እግዚአብሔር ስለ እግዚአብሔር የሚናገርበት ስለሆነ።

ስንሰማም ደግሞ እናመስግነው። እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ሲያደርግ ከማመስገን ውጪ ሌላ የሚመጥን መንገድ የለንም። ወደ እግዚአብሔር ሉአላዊ ውቅያኖስ ስንገባ ለነፍሳችን የሚሆነው ይህ ነው።

እግዚአብሔር ሆይ በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን የአንተ ስለሆነ እናመሰግንሃለን።

“ከእኔ ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለም። ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእኔ የተሾሙ ናቸው” (ሮሜ 13፡1)

“አንተም ጲላጦስ ከእኔ ካልተሰጠህ በቀር በልጄ ላይ ምንም ሥልጣን ባልነበረህም” (ዮሐንስ 19፡11)

በነፃነትህ የወደድከውን እና ያሰብከውን ስለምታደርግ እግዚአብሔር ሆይ በመገረም አለን

“በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ የወደድኩትን ሁሉ አደርጋለሁ” (መዝሙር 135፡6)

“እንደ ፈቃዴ ምክር እና አሳብ ሁሉን እሠራለሁ” (ኤፌሶን 1፡11) 

“እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም። በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ” (ኢሳያስ 46፡9-10)

ይህንን ሥልጣንህን እና ግዛትህን ከልጅህ ጋር ስለምትጋራ እግዚአብሔር ሆይ እንደነቃለን

“ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ለልጄ ኢየሱስ ሰጥቼዋለሁ” (ማቴዎስ 28፡18)

“ልጄን እወደዋለሁ ሁሉንም በእጁ ሰጥቼዋለሁ” (ዮሐንስ 3፡35)።

“በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣንን ሰጥቼዋለሁ” (ዮሐንስ 17፡2)

“ሁሉን ከልጄ እግር በታች አስገዝቼለታለሁ። ከእኔ በቀር ሁሉንም ነገር” (1 ቆሮ 15፡27)

“ልጄንም ከሙታን አሥነስቼ ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኜ አስቀመጥሁት. . . . ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛሁለት” (ኤፌሶን 1፡20-22)

“ልጄን በመንግስተ ሰማይ ተቀብዬው መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም ተገዝተውለት በቀኜ አለ። (1 ጴጥሮስ 3፡22)

በልጅህ መሪዎችን ትሽር እና ታወርድ አለህና እግዚአብሔር ሆይ በፍርሀት ላንተ እንገዛለን

ጥበብና ኃይል ለእኔ ነው። ጊዜያትንና ዘመናትን እለውጣለሁ ነገሥታትን አፈልሳለሁ፥ ነገሥታትንም አስነሣለሁ

“የነገሥታትንም እስራት እፈታለሁ፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ አስራቸዋለሁ” (ኢዮብ 12፡18)

“ክብርን ስላልሰጠኝ መልአክን ላክሁ መታውም በትልም ተበልቶ ሞተ” (ሐዋርያት ሥራ 12፡23)

አዎን እግዚአብሔር ሆይ መሪዎችን መሻር እና ማውረድ ብቻ ሳሆን በዘመናት ሁሉ ሥራቸውን ትገዛለህ።

“የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእጄ ነው ይላል እግዚአብሔር ወደ ወደድኩትም አዘነብለዋለሁ”። ምሳሌ 21፡1

“የግብጽን ብዛት በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ እሽራለሁ . . . . የግብጽን ቀንበር በዚያ እሰብራለሁ የኃይልዋንም ትዕቢት ይጠፋባታል . . . . ባቢሎንንም ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ የፈርዖንን ክንድ ግን እሰብራለሁ” (ሕዝቅኤል 30፡10 ፤ 18 ፤ 24)     

አሁንም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባሪያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ ይገዙለትም ዘንድ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ። የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጅ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን ያስገዙታል። (ኤርሚያስ 27፡ 6-7)

“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል። እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፥ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል። አሦርን በምድሬ ላይ እሰብረዋለሁ፥ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ ቀንበሩም ከእነርሱ ላይ ይነሣል፥ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል” (ኢሳያስ 14፡24-25)

“ለልጄ አሕዛብን ለርስቱ የምድርንም ዳርቻ ለግዛቱ እሰጠዋለሁ። በብረት በትር ይጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ይቀጠቅጣቸዋል” (መዝሙር 2፡8-9)

እግዚአብሔር አንተ በማይለካ ጥበብህ ከፈቀድከው ውጪ ማንኛውም ሀሳብ እንደማይሳካ በመደነቅ እናምናለን

“የአሕዛብን ምክር አጠፋለሁ፥ የአሕዛብንም አሳብ እመልሳለሁ” (መዝሙር 33፡10)

“ጥበብ ወይም ማስተዋል ወይም ምክር በእኔ ላይ የለም” (ምሳሌ 21፡30)

እግዚአብሔር ሆይ ማንም ሰው ፣ ማንም ህዝብ ፣ ምንም የተፈጥሮ ኃይል ሃሳብህን ሊከለክል አይችል ዘንድ እንዴት ኃያል እና ጠቢብ ነህ

“ሃሳቤ ይከለከል ዘንድ ከቶ አይቻልም” (ኢዮብ 42፡2)

“በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዴ አደርጋለሁ እጄንም የሚከለክላት ወይም ምን ታደርጋለህ? የሚለኝ የለም” (ዳንኤል 4፡35)

“ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው?” (ኢሳያስ 43፡13)

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በሚዛን ላይ እንዳለ ትቢያ በፊትህ እንደፋለን ከአንተ ጋር ስንወዳደር ምንም እንዳልሆንን በደስታ እናውጃለን

“እነሆ፥ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፥ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል. . . . አሕዛብ ሁሉ በፊቴ እንዳልነበሩ ናቸው ከምናምን እንደሚያንሱ፥ እንደ ከንቱ ነገርም ቆጥሬአቸዋለሁ” (ኢሳያስ 40፡15 ፤ 17)

“በምድር ክበብ ላይ እቀመጣለሁ፥ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ መጋረጃ እዘራለሁ እንደ ድንኳንም ለመኖርያ እዘረጋቸዋለሁ። አለቆችንም እንዳልነበሩ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የማደርጋቸው እኔ ነኝ” (ኢሳያስ 40፡ 22-23)

የተስፋችን ደስታ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ደካማውን በማንሳት ትዕቢተኛውን በማውረድ ታላቅነትህን ስታጎላ ነው።

“ማንኛው ሰው ነው ንጉሡን፦ በደለኛ ነህ፥ መኳንንቱንም ክፉዎች ናችሁ ሊል የሚችለው? እነርሱ ሁሉ የእጆቼ ሥራ ናቸውና በአለቆች ፊት አላደላም፥ ባለጠጋውንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አልመለከትም (ኢዮብ 34፡18-19)

“ታላላቆችን ያለ ምርመራ እሰበስባለሁ፥ በእነርሱም ፋንታ ሌሎችን አቆማለሁ” (ኢዮብ 34፡24)

“ትዕቢተኛውንም ሁሉ እመለከታለሁ፥ ዝቅ ዝቅም አድርገዋለሁ በደለኞችንም ወዲያውኑ እረገጣቸለሁ” ኢዮብ 40፡12

“እኔ እግዚአብሔር እገድላለሁ አድናለሁም ወደ ሲኦል አወርዳለሁ፥ አወጣምለሁ። ድሀ አደርጋለሁ፥ ባለጠጋም አደርጋለሁ አዋርዳለሁ፥ ደግሞም ከፍ ከፍ አደርጋለሁ” (1 ሳሙኤል 2፡6-7)

“ትዕቢተኞችን በልባቸው አሳብ በትኛለሁ፤ ገዥዎችን ከዙፋናቸው አዋርጃለሁ፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጌአለሁ” (ሉቃስ 1፡51-52)

አቤቴ እግዚአብሔር ሆይ በልጅህ ለሚያምኑት ስትል በሁሉ ላይ በዘላለማዊ ግዛት ትገዛለህ ይህም ለዘላለም ይሆናል

“ግዛቴ የዘላለም ግዛት ነውና፥ መንግሥቴም ለልጅ ልጅ ነው” (ዳንኤል 4፡34)

“ግዛቴም የማያልፍ የዘላለም ግዛት ነው፥ መንግሥቴም የማይጠፋ ነው” (ዳንኤል 7፡14)

“ልጄ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም” (ሉቃስ 1፡33)

ስለዚህ በደስታ አድናቆት እና በምስጋና በመሞላት አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ በሕይወታችን ላይ ባለው ሉአላዊነትህ እናርፋን። “ዘመናችሁ ያለው በእጄ ነው” (መዝሙር 31፡15) ስትል ስንሰማ ሐሴት እናደርጋለን።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %903 %2016 %23:%Dec
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

ከአዕምሮ እውቀት ወደ ልብ ትግበራ መሄጃ 5 መንገዶች

አንዳንድ ጊዜ ለሰዎች ከዛ በፊት ሰምተውት የማያውቁትን አዲስ ሃሳብ ታካፍሏቸዋላችሁ። ከዛም ይህ ሃሳብ ስለራሳቸው ወይንም ስለሌሎች ምናልባትም ስለ እግዚአብሔር...

Josh Squires - avatar Josh Squires

ጨርሰው ያንብቡ

ጳውሎስ ነፍሰ ገዳይ እንዲሆን እግዚአብሔር ለምን ፈቀደለት

ጳውሎስ ገና ከመወለዱ በፊት እግዚአብሔር ለሐዋርያነት እንደለየው እናውቃለን። “ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.