Thursday, 25 April 2024

ኃጢያት

  • ወደ ሮሜ ሰዎች 5:8

    ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። 

  • 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:9

    በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። 

  • መፅሐፈ ምሳሌ 1:10

    ልጄ ሆይ፥ ኃጢያተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።

  • መጽሐፈ ምሳሌ 10:28

    የጻድቃን አለኝታ ደስታ ነው፤የኀጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል። 

  • ወደ ሮሜ ሰዎች 6:23

    የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።

  • 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:8

    ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።

  • የያዕቆብ መልእክት 5:20

    ኃጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልስ ሰው ነፍሱን ከሞት ያድነዋል፤ 

  • ወደ ሮሜ ሰዎች 6:10

    ለኃጢአት እንደ ሞታችሁ ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደሆናችሁ ራሳችሁን ቁጠሩ።

  • የሉቃስ ወንጌል 7:48

    እርስዋንም :- ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል አላት ። 

  • 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:15

    ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.