አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ። (መዝሙር 51፡10-12)
ሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች በምድር ሳሉ በሥጋቸው ውስጥ ቀሪ ኃጢያት እንዳለባቸው ማወቅ እረፍት የሚሰጥ ደግሞም ልብ የሚሰብር ጉዳይ ነው።ታላቁ ሐዋርያ ሲጽፍ “አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ።” (ፊልጵስዩስ 3:12) በሌላ ቦታ ሲናገር “ነገር ግን በብልቶቼ ከአእምሮዬ ሕግ ጋር የሚዋጋውንና በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝን ሌላ ሕግ አያለሁ” (ሮሜ 7፡23) ይላል። ኢየሱስም በየዕለቱ ስንጸልይ “በደላችንን ይቅር በለን” (ማቴዎስ 6፡12) እንድንል ያስተምረናል።
Daily Injera is a Christian ministry which delivers a verse from The Holy Bible each day.
The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.