ዓለም ስለአዳኟ እና እሱን የማግኛው መንገድ ሊነገራት ይገባል ። መጽደቅ በእምነት ብቻ መሆኑ የፕሮቴስታንቶች የመድረክ ላይ ምስክርነት በላይ መሆን አለበት ። ከእዚህም ዋነኛ እውነት ጋርም ሌሎቹ የጸጋ አስተምህሮዎች ተያይዘው ቢነገሩ ለቤተ ክርስቲያናችም ሆነ ለዘመናችን የተሻለ ይሆናል ።
ያልተወሳሰበውን ወንጌልን እንጂ ፍልስፍናን እንድናውጅ አልተጠራንም ። የሰው ልጅ መውደቅ ፣ የአዲስ ውልደት ማስፈለጉ ፣ በስርየት የሆነ ይቅርታ እና በእምነት የሆነ ድኅነት እነዚህ የጦር እቃዎቻችን ናቸው ።
እነዚህን እውነቶች እንዳንማር እና እንዳናስተምር የሚያደርጉ ብዙ ነገሮች አሉን። ከተልዕኳችን ሊያዘናጋን የሚፈልግ ትምህርት ወይንም በዚህ ሩጫ ላይ ሽባ የሚያደርገን ቸልተኝነት የተረገመ ይሁን ።
Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe