Monday, 15 July 2024

የጋብቻዎን ቀን ያለ ድንግልና ማሳለፍ

Posted On %PM, %14 %500 %2016 %14:%Jul Written by

አንድ ወጣት የሚከተለዉን ጥያቄ አስተላልፎልናል፡-

ፓስተር ጆን፣ የሴት ጓደኛዬን እንድታገባኝ ልጠይቃት እፈልጋለሁ። ለትዳርም በምዘጋጅበት ጊዜ የቀደሙት ስህተቶቼ ወደ አዕምሮዬ ይመጣሉ። ከመዳኔ በፊት አብሬአቸሁ የተኛኋቸው ሴቶች እና ጌታ ቢፈቅድ አሁን ከማገባት ሴት ጋር የሰራኋቸውን ስህተቶች ወደኋላ ተመልሼ አስባለሁ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ለትዳር መጠበቅ ስላለበት ንፅህና ይህንንም ማባከን እንዴት አስከፊ እንደሆነ ይናገራሉ። እንደኔ ላሉ ከዝሙት ጋር በተያያዘ ፀፀት ለሚኖሩ ወንድና ሴቶች ምን አይነት እውነት ልታካፍለን ትችላለህ?

ፓስተር ጆን የሰጠው ምላሽ እንደሚከተለው ይቀርባል፡-

በዋነኝነት መናገር ምፈልገው ድንግልናህን ለእጮኛህ ልትሰጣት የማትችለው እሷም ላንተ ልትሰጥህ የማትችለው የከበረ ነገር መሆኑን ነው። የሚያሳዝን ትልቅ እጦት ነው።

ይሁን እንጂ ማጣታቸሁ የከፋ እንዳይሆን እግዚአብሔር በእጅጉ ሊያበዛው የሚችል ስጦታ ልትሰጣት ትችላለህ።

ሰዎች ሩካቤ ሥጋን ለትዳር ስለመጠበቅ ይህንንም ማባከን አስከፊ እንደሆነ ሲያወሩ እንደሰማህ ተናግረሃል። እኔም አዎን ልክ ናቸው እላለሁ። ጳውሎስ እና ኢየሱስ ለአንድ ድንግል የሚመክሩት ይህንኑ ነው ብዬ አስባለሁ። “ከዝሙት ሽሹ” (1 ቆሮንቶስ 6፡18)

ባላገባህበት ጊዜ ሥጋህ የእግዚአብሔር ነው። ደግሞም የወደፊት የሚስትህ ይሆናል። ስለ 1 ቆሮንቶስ 7፡3-4 ማሰብ መልካም ይሆናል፡- “ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት” — ሩካቤ ሥጋን ማለቱ ነው — “ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ። ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።”

በሌላ አገላለፅ አንዳቸሁ ለአንዳቸሁ ብቻ ነው የምትገቡት። ሌላ ለማንም አይደለም። ባላገባችሁባቸው ወቅቶች በመንፈሱ አማካኝነት በሥጋችሁ ከእግዚአብሔር ጋር አብራችሁ ለእርሱ የተገባችሁ ናችሁ። በትዳር ጊዜ ደግሞ ከትዳር አጋራችሁ ጋር አንድ በመሆን ለእግዚአብሔር የተገባችሁ ናችሁ። ይህ የከበረ በትዳር ውስጥ ሊሰጥ የተገባ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ስጦታ ነው።

ያ መስጠት ያለብህ ስጦታ አይደለም። ልጆችህ እንዲኖራቸው ልታስትምራቸውም ትፈልጋለህ።

እንግዲህ ወሲባዊ ግንኙነት ለነበራችሁ እጮኛህ ልትሰጣት የሚገባህ ስጦታ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ተደስቶበት አስደናቂ እንዲሆን በማድረጉ ምክንያት ልትሰጣት ያልቻልከው ያ ስጦታ የማያጠፋው ምን ስጦታ ልትሰጣት ትችላለህ?

ይህንን ልትሰጣት ትችላለህ። እጮኛህን እንዲህ ልትላት ትችላለህ፡-

በእግዚአብሔር ፊት ከሚጠበቅብኝ ጎድያለሁ። በአንቺም ፊት ከሚጠበቅብኝ ጎድያለሁ። ለዚህም የእውነት የሆነ ጥልቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ያደረግሁትን ነገር እጠላዋለሁ። በአንቺም ላይ ሆነ በእኔ ላይ ያደረሰብንን ጉዳት እጠላዋለሁ። በእግዚአብሔር ላይ ያመጣሁትን ሀፍረት እጠላዋለሁ። ለአንቺ የተሻለዉን ባለመምረጥ እንደሚገባሽ አለማክበሬን እጠላዋለሁ። ለዚህም ንሰሃ እገባለሁ።

ከዚህም ኃጢአት ሆነ እንዳረገው ከሚገፋፉኝ ነገሮች እራሴን መልሻለሁ። ሁሉንም ትቻቸዋለሁ። ወደ ጌታዬና መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሴን እመልሳለሁ፤ በደሙ የተገዛውን ሙሉ ይቅርታም ትልቅ ዋጋ ሰጥቼ በሙሉ ልቤ እይዘዋለሁ።

ደሙን ማክፋፋት አሁን ያስፈራኛል። በሰጠኝም በመንፈሱ መቼም ቢሆን ላልክደውም ሆነ ሥጋዬን ከሚስቴ ውጪ ለማንም ላልሰጥ በሰጠኝ በዚህ ሃይል ቆርጫለሁ።

ታላቅ ዋጋ ሰጥቼ ላከብርሽ እና ታማኝ ልሆንልሽ ይቅር የተባለ እና የተቤዠ ነፍሴን ለትዳር እሰጥሻለሁ። ወደዚህ አዲስ ወደ ሆነ ይቅር ወደተባለ ወደተቤዠ የነፃ ህብረት እጋብዝሻለሁ። ጠባሳውና ትውስታው ሁሌ እንደሚኖሩ አውቃለሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ በጥበቡና በራሱ መንገድ ይህንን የኃጢአት ጠባሳ የምሕረቱ አርማ እና የመስቀሉ ምልክት ያደርገዋል። ይህ ለእጮኛህ ልትሰጣት የምትችለው ታላቅ ስጦታ ነው። እግዚአብሔር ይህንን ስጦታ እንዲያትምላችሁ እጸልያለሁ።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %10 %825 %2016 %21:%Dec
Tony Reinke

Tony Reinke is a staff writer for Desiring God and the author of three books: 12 Ways Your Phone Is Changing You (2017), Newton on the Christian Life: To Live Is Christ (2015), and Lit! A Christian Guide to Reading Books (2011). He hosts the popular Ask Pastor John podcast, and lives in the Twin Cities with his wife and three children.

twitter.com/TonyReinke

ኢየሱስ ያድናል

“የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” (ሉቃስ 19፡10) ክርስትና “ኢየሱስ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና” በሚሉት ቃላት ሊጠቃለል ይች...

Jonathan Parnell - avatar Jonathan Parnell

ጨርሰው ያንብቡ

ምኞትን ለመዋጋት የሚጠቅሙ ስልቶች

ይህን ስጽፍ ወንዶችንም እና ሴቶችንም በማሰብ ነው። ለወንዶች በእርግጥ ግልጽ ነው። በወሲባዊ ምስሎች የሚመጣ ፈተናን ለማጥፋት የሚደረግ ውጊያ አስፈላጊ ነው። ...

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.