Thursday, 25 April 2024

መዳን

  • የማቴዎስ ወንጌል 24:13

    እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።

  • ትንቢተ ኢሳይያስ 30:15

    በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥

  • መዝሙረ ዳዊት 18:3

    ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ። 

  • 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:23

    ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።

  • ትንቢተ ኢሳይያስ  59:1

    እነሆ፥ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፥ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም፤

  • ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:8

    ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤

  • ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:4-5

    ነገር ግን በምሕረቱ ባለጠጋ የሆነ እግዚአብሔር ለኛ ካለው ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ፤በበደላችን ሙታን ሆነን ሳለ፤ በክርስቶስ ሕያዋን አደረገን፤

  • ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:22

    አሁን ግን ነውር ነቀፋ የሌለባቸሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፤ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።

  • 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:15

    ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.