Saturday, 18 May 2024

ላለፈ ሕይወታችሁ ባሮች አይደላችሁም Featured

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ክርስትና፣" ለውጥ ይቻላል" ማለት ነው። ጥልቅ የሆነ መሠረታዊ ለውጥ። ቀድሞ ልበ ደንዳኖች እና ደረቅ ልቦች ከነበራችሁ አሁን ልበ ሩህሩህ መሆን ትችላላችሁ። በመራርነት እና ቁጣ ቁጥጥር ስር አለመሆን ይቻላል። ያለፈ ታሪካችሁ ምንም ቢሆን መውደድ የምትችሉ ሰዎች መሆን ትችላላችሁ።

መጽሐፍ ቅዱስ መሆን ያለብንን የሚወስነው እግዚአብሔር እንደሆነ ይነግረናል። መጽሐፍ ቅዱስ በሚገርም ግልጽነት ሲናገር “ክፋትን ሁሉ አስወግዳችሁ ርኅሩኆች ሁኑ ይላል”። “ብትችሉስ ርኅሩኆች ሁኑ አይደለም የሚለን”። ወይንም “ወላጆቻችሁ ለእናንተ ርኅሩኆች ከነበሩ . . .” ወይንም “ችግር ኖሮባችሁ ወይንም ተበድላችሁ የምታውቁ ካልሆነ. . .” አይልም ነገር ግን “ርኅሩኆች ሁኑ” ነው የሚለው።

ይሄ በሚያስደንቅ መልኩ ነፃ ያወጣናል። አንዴ ተወስኗል ለውጥ ማምጣት የማይቻል ነገር ነው ብሎ ከማመን መጥፎ አስተሳሰብ ነፃ ያወጣናል። ያለፈ ታሪካችን መጨረሻችን ነው ብሎ ከሚያምንም አስተሳሰብ ነፃ ያወጣናል።

እስረኛ ብሆን እና ኢየሱስ ወደታሰርኩበት ክፍል መጥቶ “ይሄን ቦታ ዛሬ ማታ ለቅቀህ ውጣ” ቢለኝ ግራ ልጋባ እችላለሁ ነገር ግን መልካምነቱን እና ኃይሉን የማምን ከሆነ ነፃነት የሚቻል ነገር እንደሆነ ተስፋ ይሰማኛል። ካዘዘ ሊያደርገው ይችላልና። 

ሌሊት ቢሆን እና ማዕበሉ በኃይል እየተናወጠ ኢየሱስ ወደ እኔ መጥቶ “ነገ ጠዋት ወደ ማዶ እንሻገራለን” በዚያ ለሊት ተስፋ ይፈነጥቃል። እርሱ እግዚአብሔር ነው። የሚያደርገውን ያውቃል። ትዕዛዞቹን ለማለት ያህል የሚላቸው ቃሎች አይደሉም።

ትዕዛዞቹ ነፃ ከሚያወጡ ሕይወትን ከሚቀይር እዉነት ጋር ነው የሚመጡት። ለምሳሌ 

እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ [ይሄ ትዕዛዝ ነው] ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ [ይሄ ደግሞ ሕይወትን የሚቀይር እውነት] ይቅር ተባባሉ። እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች [ሌላ ሕይወትን የሚቀይር እውነት] እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ [ሌላ ትዕዛዝ] ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ [ሌላ ሕይወትን የሚቀይር እውነት] በፍቅር ተመላለሱ [ሌላ ትዕዛዝ]። (ኤፌሶን 4፡32-5፡2)

በእነዚህ ቃሎች ውስጥ ሕይወትን የሚቀይር ኃይል አለ። እስቲ ይህ ኃይል እንዲቀይራችሁ እየጸለያችሁ ከኔ ጋር አሰላስሏቸው ።

1. እግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ አድርጓችኋል

አዲስ አባት እና አዲስ ቤተሰብ አለን። ይሄ በዕድል የሚያምኑትን የቤተሰብ አመጣጥ ይሰብራል። “አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ” (ማቴዎስ 23፡9)።

አንድ ጊዜ አንድ ወጣት ልጅ እግዚአብሔርን እንደ አስቸጋሪው አባቱ ሊያስብ እንደማይገባው ያሳመነውን ዕብራውያን 12፡10-11 እንባ ባዘሉ ዓይኖች እና በታላቅ ደስታ ሲጠቅስ ሰምቼዋሁ። 

እነርሱ (የምድር አባቶቻችንን) መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል። (ዕብራውያን 12፡10-11)

እነእርሱ ይህን አደረጉ. . . እርሱ ግን ያንን አደረገ። ይሄ እውነትን የሚቀይር እውነት ነው። ምንም አይነት ምድራዊ አባቶች ቢኖሩን ይህን እውነት ልናውቀው ፣ ልናምነው እና ልንቀየርበት እንችላለን። እግዚአብሔር ስለ አባትነቱ ያለንን አስተሳሰብ ለመገለባበጥ እራሱን በቃሉ ገልጾልናል። እንደ ሌሎች አመጣጣችን የተበላሸ ነው ብለን ማሰብ የለብንም።

2. እግዚአብሔር እኛ ልጆቹን ይወደናል 

እኛ “የተወደዱ ልጆች” ነን። የእግዚአብሔርን ፍቅር እንድናስተጋባ የተሰጠን ተዕዛዝ እንዲሁ በአየር ላይ ያለ ሳይሆን “እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች” ከሚል ኃይል ጋር የመጣ ነው። ትዕዛዙ “ውደዱ” ነው ኃይል የሚሆነን ደግሞ “መወደዳችን” ነው።

3. እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር ብሎናል

እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። እግዚአብሔር ለእኛ ያደረገልን ለመለወጥ ኃይል ይሆነናል። ይቅር ብሎናል። ይሄ የፍቅር ግንኙነትን እና የወደፊት ተስፋን ይከፍታል። ርኅሩኅ መሆን ሳይገባን በመወደዳችን ምክንያት ከሚትረፈረፍ ልብ እና ለዘላለም ከመጠበቃችን ምክንያት አይፈስምን? ርኅሩኆች እንድንሆን የተሰጠን ትዕዛዝ እግዚአብሔር ከእናት እና አባታችን በላይ ካደረገልን የሚበልጥ ነገር የዘለለ ነው። ላለፈ ሕይወታችሁ ባሮች አይደላችሁም።

4. ክርስቶስ ወዷችኋል እራሱንም ስለእናንተ ሰጥቷል

“ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ በፍቅር ተመላለሱ”። በፍቅር እንድንመላለስ የተሰጠን ትዕዛዝ እንደተወደድን ከሚገልጽ ሕይወትን ከሚቀይር እውነት ጋር ነው የመጣው። እንድትወዱ ዕድል በምታገኙባቸው ጊዜያት ማንኛውም ድምጽ መጥቶ “አንተ እኮ መውደድ የምትችል ሰው አይደለህም” ቢላችሁ እንደዚህ በሉት “ክርስቶስ ለእኔ ያለው ፍቅር አዲስ ሰው አድርጎኛል። እንድወድድ የሰጠኝ ትዕዛዝ እንደሚወደኝ እንደሰጠኝ ተስፋ ሁሉ እርግጥ ነው።”

ልመናዬ፣ ነገሮች አንዴ ከሆኑ በኋላ ሊቀየሩ አይችሉም የሚለውን አስተምህሮ በመሉ አቅማችሁ እንድትፋለሙት ነው።  ለውጥ የሚቻል ነገር ነው። በክርስቶስ መምጣት ፍጹማን እስክትሆኑ ድረስ ፈልጉት።

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %AM, %23 %926 %2017 %00:%Jan
John Piper

John Piper is founder and teacher of desiringGod.org and chancellor of Bethlehem College & Seminary. For 33 years, he served as pastor of Bethlehem Baptist Church, Minneapolis, Minnesota. He is author of more than 50 books, including A Peculiar Glory.

twitter.com/JohnPiper

ጾም ለጀማሪዎች

ምንአልባት አልፎ አልፎ አልያም ፈጽሞ ከማይጾሙት ብዙኃኑ የክርስቲያን ጎራ ልትሆኑ ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱሳችንን ስላላነበብን ወይንም ከአንድ ሊታመን ከሚገባ ...

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

ምስጋና ለመስጠት 32 ምክንያቶች

እንግሊዛዊው ፓስተር እና የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኝ ማቲው ሄነሪ (1662-1714) ከመሞቱ 2 ዓመት በፊት ስለ ጸሎት መጽሐፍ ጽፎ ነበር። ለጸሎት የሚሆን መንገድ...

Donny Friederichsen - avatar Donny Friederichsen

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.