Saturday, 04 May 2024

ከፓርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል!

በአንድ ወቅት ‘ጉግል’ አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሐገራት መካከል እናንተ ኢትዮጵያውያን ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር። በዚች ሀይማኖታዊ በሆነችው ሀገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው የፖርኖግራፊ ተጠቃሚ ወይም በፖርኖግራፊ ሱስ ተጠቂ ነው። ይህ በሀገራችን ብዙ የማይደፈር ርዕስ ቢሆንም፣ ስለ ፖርኖግራፊ ሱስ ምንነት፣ ምልክቶች፣ መዘዞች እና መውጫ መንገዶቹ ትውልድንም፣ ራሳችንንም ለማዳን ስንል ደፍረን ልንነጋገርበት ወስነናል። አብራቹን ቆዩ!

Start the Series

ጽናት - ከሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻ የምድር ላይ ጊዜያት የምንወስደው ትምህርት

‹አንተ ግን … ጽናቴን ሁሉ ታውቃለህ› 2ኛ ጢሞ 3፡10

የሐዋርያው ጳውሎስ የዕለት ተዕለት ሕይወት እና አገልግሎት በከባድ ኩነቶች የተሞላ ነበር። ይበልጥ ደግሞ በአገልግሎቱ የመጨረሻ ጊዜያት ማለትም በሁለተኛው የሮሜ እስራቱ ወቅት ሕይወቱ እና አገልግሎቱ እጅግ ፈታኝ እና እጅግ ከባድ ሁኔታ ውስጥ ነበር። ሐዋርያው በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት በጽናት እምነቱን ጠብቆ ሩጫውን የፈጸመ ታላቅ የእምነት አርበኛ ነው። በቀጣዮቹ ስምንት ቀናት ከሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻ ቀናት ገጠመኞች ውስጥ በጽናት ስላለፋቸው ተግዳሮቶች የሐዋርያውን የመጨረሻ ደብዳቤ የሆነውን 2ኛ ጢሞቴዎስ መልዕክትን ተንተርሰን እንማራለን። በዚህም ለእግዚአብሔር መንግስት በሚኖረን አገልግሎት እንዲሁም በዕለት-ተዕለት የክርስትና ጉዟችን የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች በጽናት ለማለፍ አቅም እንደምናገኝ እምነቴ ነው።

ጳውሎስን ከጎኑ ቆሞ ያበረታ እና ያጸና አምላክ (ሐዋ 23፡11) እኛንም ያበርታን ደግም ያጽናን! አሜን

Start Plan

ከትንሳዔው ማግስት

ቤተክርስትያን ስላለችበት ሁኔታ እንዲሁም በውስጧ እየሆኑ ስላሉት ስብራቶችና ግራ የሚያጋቡ ነገሮች ስናይ "'ኧረ መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው?' የሚል ጥያቄ አይፈጠርባችሁም? ክርስቶስ የሞተውና የተነሳው 'ለዚህ ነው?' አያስብላችሁም? በሚቀጥሉት 5 ቀናት ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ 'መንፈሳዊነት ምን ማለት ነው?' የሚለውን ከሳምሶን ጥላሁን ጋር፣ ከዚያም ስለትንሳዔ እና አዲስ ሕይወት ከናዖል በፍቃዱ ጋር ለ4 ቀናት በማየት የሚያዝያን የ'አዲስ ጅማሬ ወር'ን እንዘጋለን።

Start Plan

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.