Sunday, 19 May 2024

የእምነት ጉዳይ ነው

Posted On %PM, %07 %845 %2016 %22:%Dec Written by

በዚህ በሚታየው እና በሚጨበጠው ቁስ ተኮር እና ስግብግብ ዓለም ውስጥ ስንኖር ለእኛ የሚያሳስቡን ነገሮች ለእግዚአብሔር ከሚያሳስቡት ነገሮች ጋር በፍጹም የተለያዩ ናቸው።

ለእግዚአብሔር የሚያሳስበው ህዝብ ነው።

ውጪያዊ ገጽታ አይስበውም።

የሀብት ክምችት አይስበውም።

የሚስበው ልብ ነው።

በልቡ ጥልቀት ውስጥ ደግሞ ያለው ከመታወቅ የሚያልፍ ፍቅር ነው።

ለእርሱ ያለን ፍቅር ወደ እርሱ እንድንቀርብ ያደርገናል። ለእርሱ ያለን የፍቅራችን መጽናት ደግሞ ቃሉን እና መንገዱን ለማመን ያለን ብቃታችን ነው።

የእምነት ጉዳይ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ሲናገር ያለዚህ ቀላል ነገር እግዚአብሔርን ማስደሰት እንደማይቻል ነው።

"ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።" (ዕብራውያን 11፡6)

ሚስዮናዊ ሆኜ ወደ ኢትዮጲያ ስመጣ ያለኝን ጉዞ ሳስብ እግዚአብሔር በእኔ ውስጥ በዋነኝነት ሊያደርገው ይገባ የነበረ ነገር እምነቴን መጨመር ነበር። ጌታ ሆይ እምነት ጨምርልን! ብለን ጮህን። እርሱም ጨመረልን። የምናደርገውን ሁሉ የምናደርገው ሁሉንም እኩል በፈጠረ ደግሞም በአምሳሉ ስለፈጠራቸው ፍጥረቶቹ ያለውን ልብ እንዲያውቁ በሚፈልግ አምላክ ስለምናምን ነው።

ስለዚህ ለእኔ ያለውን ልብ ማወቅ አለብኝ።  

በህይወት ዘመኔ ሁሉ ከፍርኃት ጋር የነበረኝ ትግል ከአንድ ነገር ጋር የነበረ ትግል ሳይሆን ከአንድ ነገር ጋር የነበረ የተቃርኖ ትግል ነው። ከፍርኃት ጋር የነበረኝ ትግል በዋነኝነት ከእምነት ጋር የነበረኝ የተቃርኖ ትግል ነበር።  

እንዳታሸንፉ አለመፈለግ ብቻ ሳይሆን መሸነፍም አይፈልግም…

በውጊያውን እንደተሸነፈ አስቀድሞ አውቋል፣ ነገር ግን የነጥብ መያዣ ወረቀቱን እንደማናይ ያውቃል። ሀሳባችን ሙሉ ያለው በጨዋታው ላይ ነው። ሀሳባችንን ሁሉ ኳሱ ላይ እንድናደርግ በማድረግ አምታቶናል። እኛም ላለመሸነፍ ከመጠን በላይ እንባትላለን። ነገር ግን ቀድሞውንም ተሸንፏል።

ስለዚህ ልጅ እያለሁ የሞት ፍርኃት፣ በወጣትነት ዘመኔ ደግሞ የመገፋት ፍርኃት፣ የመቀጣት ፍርኃት፣ ብቸኛ የመሆን ፍርኃት… እነዚህ ሁሉ እምነት እንዳይኖረኝ ሽባ አድርገውኝ ነበር።

ፍርኃት የእምነት ተቃራኒ ሳይሆን የእምነታችን ጠላት ነው። ጭንቀት፣ ስጋት፣ አለመተማመን ፣ ሽብር ሁሉ የፍርኃት ጓደኞች እና አበሮቹ ናቸው።

ነገር ግን ፍርኃትን አውጥተን ልንጥልበት ደግሞም ልናሸንፍበት የምንችለው መሣሪያ ፍጹም ፍቅር ነው።  


ፍርኃት የእምነት ተቃራኒ ሳይሆን የእምነታችን ጠላት ነው። 


"ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።"(1 ዮሐንስ 4፡18)

እናም ወደ ህይወቴ ፍፁም ፍቅር መጣና ከፍርኃት ነፃ አውጥቶ እምነት እንዲኖረኝ አቅምን ሰጠኝ። ፍርኃት ተወግዶ እምነት ገባ። ለሊት በሆነ ጊዜ ጉሮሮዬን አንቀው የሚይዙ ጭንቀቶቼ ፣ ልቤን በቁጭት ሞልቶ የነበረው ስቃይ እና ወደፊት እርምጃ የመውሰድ ችሎታዬን ይዞ የነበረ ጥልቅ ፍርኃት በአንድ ሌሊት በነው ጠፉ።

ታዲያ ፍርኃት እንዲያሸንፍ ስንፈቅድለት ምን ይሆናል?

ሙሴ ውሃ እንዲሰጣቸው ይለምኑት የነበሩ ከግብጽ ምድርም በምድረበዳ እንድንሞት አወጣኸን እያሉ የሚያጉረመርሙበት ብዙ ተከታዮች ነበሩት። እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ ከውስጡ ውሃን ያወጡ ዘንድ ድንጋይን አዘጋጀላቸው። እግዚአብሔር ድንጋዩን ተናገረውና ከውስጡ ውሃ ይወጣል አለ።

ነገር ግን ሙሴ ድንጋዩን መታው። ብዙ ጊዜ እንደምናደርገው አደረገ። ተአምራቱን ወደራሱ እጅ ወስዶ ከማመን ይልቅ የራሱን ፍቃድ አደረገ። እግዚአብሔር ያለው መንገድ ላይሰራ ይችላል፣ ሰዎቹም ችሎታዬን አያከብሩትም ብሎ በማሰብ ህይወትን ከመናገር ይልቅ ህይወትን ሰበረ።

በዚህ ስግብግብ እና ቁስ ተኮር፣ በሥራ መጨናነቅ ፣ መግዛት፣ መበደር እና ትርፍ ማካበት በሚበረታታባት ዓለም ውስጥ ከማመን እና እምነት እንዲኖረን ከመፈለግ ይልቅ መሥራትን እንፈልጋለን።

እንደዚያ ካልሆነ ማሟላት ያለብንን አቅርቦት ማሟላት አንችልም ብለን እናስባለን። በመሠረቱ ይሄ ትዕቢትን ያስደስተዋል። ነገር ግን ውሃው እስኪወጣ ድረስ ሲመታ እንደነበር ጠንካራ ሰው ለመምሰል ስናደርግ የነበረው ኩራታችን “በእስራኤል ልጆች ፊት ትቀድሱኝ ዘንድ በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም ።” (ዘኁልቁ 20፡12) የሚል ድምጽ ስንሰማ ኩራታችን የዛኔ ይጠፋል።  

እግዚአብሔር በእምነታችን እና በእርሱ ላይ በመደገፋችን የሚደነቀውን ያህል በጥንካሬያችን ውይንም በችሎታችን አይደነቅም።

እኛ ማድረግ ብንፈልግም እርሱ ግን መሆንን ብቻ ከእኛ ይጠብቃል። ታዛዥ መሆንን። ታማኝ መሆንን።

ሙሉ እምነት አለኝ ላስፈለገኝ ነገር እንደሚያሟላ

እንደ አብርሃም ባናየውም 

እንደ ረዓብ ባይገባንም 

እንደ ሱናማዊቷ ሴት ተስፋ ብንቆርጥበትም 

እንደ ዮናስ ብንክደውም

ሙሉ እምነት አለኝ ተስፋውን ግን እንደሚፈጽም. . .

ቤታችንን በኪሳራ ስንሸጥ በሚያም ሁኔታ እምነታችን ተፈትኖ ነበር። እያደረግን ያለነው ነገር ትክክል ነው? ራስ ወዳዶች ሆነን ልጆቻችን የሚገባቸውን ርስት እየከለከልናቸው ነው? ተመልሰን የምንሄድበት ስፍራ ባለማስቀመጣችን ስህተት እየሰራን ነው? እነዚህ ሁሉ ያስጨነቃቸው ጓደኞቻችን እና ቤተሰቦቻችን ጭንቀቶች ቢሆኑም ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር ግን ለእኛ ከቤት የዘለለ ነገርን ፤ የእምነትን ህይወት ይፈልግ ስለነበር ጭንቀቶቹን ደመሰሳቸው።


ቤታችንን በኪሳራ ስንሸጥ በሚያም ሁኔታ እምነታችን ተፈትኖ ነበር። እያደረግን ያለነው ነገር ትክክል ነው? ራስ ወዳዶች ሆነን ልጆቻችን የሚገባቸውን ርስት እየከለከልናቸው ነው? ተመልሰን የምንሄድበት ስፍራ ባለማስቀመጣችን ስህተት እየሰራን ነው? እነዚህ ሁሉ ያስጨነቃቸው ጓደኞቻችን እና ቤተሰቦቻችን ጭንቀቶች ቢሆኑም ፍቅር የሆነው እግዚአብሔር ግን ለእኛ ከቤት የዘለለ ነገርን ፤ የእምነትን ህይወት ይፈልግ ስለነበር ጭንቀቶቹን ደመሰሳቸው።


ሁልጊዜ ስንሰጥ እምነታችንን እንፈትናለን። እግዚአብሔር እንደሚወርድ እና እንደሚባርከው እናምናለን። አድርጉት ይለናል።

በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ” (ሚልኪያስ 3፡10)

ተግዳሮቶችን ጥሰን ባለፍን ቁጥር እምነታችንን እንፈትናለን። እነዚህ ተግዳሮቶች የአንድ ነገር መጨረሻ አይደሉም ነገር ግን በድካማችን ፍጹም የሚሆነውን ኃይላችንን ለመጨመር የተቀመጡ የተግዳሮት መለኪያዎች ናቸው።

በምንወድቅበት ጊዜ ሁሉ እምነታችንን እንፈትናለን። ለኃጢያታችን የተከፈለው ዋጋ በመስቀል ላይ ተፈጽሟል የሚለውን እምነታችንን እና እንዲወቅሰን እንዲሁም እንዳንሰቃይበት እግዚአብሔር ሸፍኖታል ብለን ማመናችን ይፈተናል።

እንድናርፍ ሲጠበቅብን እና እንቅስቃሴዎቻችንን መግታት ሲጠበቅብን እምነታችን ይፈተናል። ከእራሳችን የበለጠ ዓላማ ያለው የአንድ ነገር ክፍል እንደሆንን ያለን እምነት ይፈተናል። በጊዜው እየሆነ ካለው ነገር የሚበልጥ ነገር። ልናደርገው ከምንችለው በላይ የገዘፈ ነገር። አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፍቅር ለማወቅ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው መገኘት ብቻውን በቂ ነገር መሆኑን ነው።

ምክንያቱም ስናርፍ ፣ ስንጠብቅ እና ስናውቅ እርሱ እንጂ እኛ እግዚአብሔር እንዳልሆንን እናውቃለን። እርሱ እንጂ እኔ ከድንጋይ ውስጥ ዉሃን ላወጣ እንደማልችል አውቃለሁ። አምልኳችንን ጸጥ ስናደርግ እንኳን ድንጋዬቹን እንዲያመልኩት ሊያስነሳ እንደሚችል እናውቃለን። ከድንጋይ ውሃንም አምልኮንም ሊያወጣ ይችላል። እኔ ግን አልችልም ስለዚህ ላምነው እችላለሁ። በእርሱ እምነት ይኑራችሁ።  

አብርሃም የሚኖርበትን ስፍራ ትቶ እንዲሄድ የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ስለታዘዘ የእምነትን ህዝብ ወለደ።

እኛም ሀገራችንን በተመሳሳይ መንገድ ትተን ወጣን። ምን እንደምናደርግ ወይንም እንዴት እንደምናደርገው ሙሉ ዝርዝሩን ሳናውቅ ደግሞም ምን አይነት ትግሎች በመንገዳችን ሊገጥሙን እንደሚችሉ ሳናውቅ መሄድ እንደነበረብን ብቻ በማወቅ ትተን ወጣን።  

በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመኖቼ ላይ “ኃጢአታችሁም እንዲያገኛችሁ እወቁ። ” የሚለውን ጥቅስ ከዘኁልቁ 32፡23 ላይ አጥኝቼው ነበር። ይህ ድንቅ ጥቅስ ከአውዱ ተነጥሎ ሲታይ አንድን ሰው ኩነኔ ያለበት ሆኖ እንዲሰማው የሚያደርግ ቢሆንም እያወራ ያለው ኃጢያት ግን በአንድ ምድር አልኖርም ብሎ ለእግዚአብሔር አልታዘዝም ስለማለት ኃጢያት ነው። የተጠራነው ለዚህ ነው። የኢትዮጲያ ምድር መኖሪያ ርስት እንዲሆንልን ነው።  

እምነት እግዚአብሔር የሚሰጠን በረከት ነው። ይህንንም በረከት ስንቀበል ጥሩ እረኞች መሆን አለብን። ፍርኃት ፣ ጭንቀት ወይንም ስጋት እምነታችሁን እንዲበክሉት አትፍቀዱ። ሥራችሁም ሊተካው እንደሚችል አታስቡ። እግዚአብሔር እግዚአብሔር እንዲሆን ፍቀዱለት።

"ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።" (ኤፌሶን 2፡8-9)

 

Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %PM, %28 %731 %2016 %19:%Dec
Michelle Zombos

Born in Auckland, New Zealand to migrant parents from Western Samoa and Australia/Greece, Michelle declared at the age of six that one day she would be a “missionary” to Ethiopia. After giving her life to Jesus as a 19-year-old mother and wife, she started to serve in ministry in South Auckland’s urban community. After having her five children and graduating from Bible College, she eventually came to Ethiopia with her family where she has served a local Ethiopian Evangelical Mekane Yesus Church in Debre Zeit and Addis Ababa. She is passionate about the word of God and sharing it with those who long to connect with their Creator.

aheartforethiopia.blogspot.com/

እየሻከረ እና እየቀዘቀዘ ያለው የሶሻል ሚድያ የክርስቲያኖች ሕብ…

‹‹እላችኋለሁም ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሃቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግስተ ሰማያት ይቀመጣሉ።›› ማቴ 8፡10-11

Naol Befkadu - avatar Naol Befkadu

ጨርሰው ያንብቡ

ከአዕምሮ እውቀት ወደ ልብ ትግበራ መሄጃ 5 መንገዶች

አንዳንድ ጊዜ ለሰዎች ከዛ በፊት ሰምተውት የማያውቁትን አዲስ ሃሳብ ታካፍሏቸዋላችሁ። ከዛም ይህ ሃሳብ ስለራሳቸው ወይንም ስለሌሎች ምናልባትም ስለ እግዚአብሔር...

Josh Squires - avatar Josh Squires

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.