Saturday, 04 May 2024

የተስፋ ነፀብራቆች ሁኑ Featured

Posted On %AM, %11 %041 %2016 %03:%Oct Written by

ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው” (1 ተሰሎንቄ 5፡11)።

ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም በሐዋርያት በርናባስ ተባለ ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ ነው” (የሐዋርያት ሥራ 4፡36)። የምታፅናኑ ሰው ከመሆናችሁ የተነሳ ጓደኞቻችሁ መጽናናት ብለው ሲጠሯችሁ የሚያሰደንቅ ነገር አይደለምን?

ጽናት የፍርሀት ዛቻን ፊት ለፊት የመጋፈጥ ውሳኔ ነው። ጽናት ደግሞ ከምንፈራው ነገር በሚበልጥ ተስፋ ይነዳል።  

አለመጽናናት ተስፋችን ሲደክም ይመጣል። በፍርሃታችን ፊት መርበድበድ እንጀምራለን። ይሄ ነገር ሲገጥመን (ደግሞም ብዙ ጊዜ ይገጥመናል) ተስፋ የሚጨምርብን ነገር ያሻናል። መጽናናት ማለት ያ ነው።"ብዙ ሰዎች መልካሙን የእምነት ገድል መጋደል ይችሉ ዘንድ" (1 ጢሞቴዎስ 6፡12) በርናባስ ተስፋን ሲጨምርባቸው ነበር።እንደ በርናባስ ያሉ ሰዎች ያስፈልጉናል። እኛም እራሳችን እንደ በርናባስ መሆን አለብን።

ያለመጽናናት ጎርፍ

የምንኖረው ያለመጽናናት ጎርፍ ውስጥ ነው። ነቀፌታ ፣ ሂስ ፣ ማረም የመሳሰሉት የዚህች የወደቀች ዓለም ቋንቋዎች ናቸው። የሰው ልጅ ልቡ በትዕቢት የተትረፈረፈ ስለሆነ የሚያጽናኑ ቃላት ከመናገር ይልቅ እንደዚህ ያሉት ቃላት በቀላሉ ከምላሱ ይወጣሉ። (ማቴዎስ 12፡34)

በኃጢያተኛው ማንነታችን እኛ የሰው ልጆች እርስ በእርስ ተነቃቅፈን እንኖራለን። ሀያሲነትን ሳይቀር የሥራ መደብ አድርገነዋል። በጋዜጣ ይሁን በኢንተርኔት አሊያም ከአጠገባችን የተቀመጡ ሰዎች ሲያወሩ የምንሰማው አብዛኛዎቹ ስለሰዎች ፣ ሀሳቦች ፣ ድርጅቶች እንዲሁም መንግስት ያሉ ወሬዎች አሉታዊ ናቸው። እርግጥ ነው ሂስ እና ነቀፌታ የሚያስፈልጋቸው ነገሮች አሉ። ነገር ግን አሉታዊ አስተያየቶች የመብዛታቸው ምክንያት እነዚህ በትዕቢት የተሞሉት የወደቀው ሰው የልቦናችን ዓይኖች የሌሎችን ድካም ፣ ጥፋት ስህተት እና ኃጢያት እንድናይ ስለሆኑ ነው። ዓይኖቻችን ይህን መፈለግ ያስደስታቸዋል። የሌለ ጥፋት ሳይቀር ያያሉ። እንደዚህ የሆንነው ለምንድን ነው?

ምፀት ቢመስልም አንዱ ምክንያት ሁላችንም ለእራሳችን ተስፋን እየፈለግን ስለሆነ ነው። መጽናናት የሚመጣው ከተስፋ ነው። አለመጽናናት ተስፋችን ሲደክም ይመጣል። ስለዚህ ኃጢያተኛው የሰው ልጅ የእራሱን አለመጽናናት እና የውድቀቱን እና ኃጢያቱን ጸጸት ለማቅለል ሲል መንገድን ይፈልጋል። የመጽናናት አምላክ (ሮሜ 15፡5) በሆነው የጸጋው ወንጌል ላይ ያለን እምነት ከልባችን ውስጥ ሲጠፋ ወይንም ሲያጥር እራሳችንን ለማበረታታት ወደሌሎች ውድቀት እና ኃጢያት እንመለከታለን።


ምፀት ቢመስልም አንዱ ምክንያት ሁላችንም ለእራሳችን ተስፋን እየፈለግን ስለሆነ ነው። መጽናናት የሚመጣው ከተስፋ ነው። አለመጽናናት ተስፋችን ሲደክም ይመጣል። ስለዚህ ኃጢያተኛው የሰው ልጅ የእራሱን አለመጽናናት እና የውድቀቱን እና ኃጢያቱን ጸጸት ለማቅለል ሲል መንገድን ይፈልጋል። የመጽናናት አምላክ (ሮሜ 15፡5) በሆነው የጸጋው ወንጌል ላይ ያለን እምነት ከልባችን ውስጥ ሲጠፋ ወይንም ሲያጥር እራሳችንን ለማበረታታት ወደሌሎች ውድቀት እና ኃጢያት እንመለከታለን።


ምክንያቱ ይሄ ስለሆነ ሊገርመን አይገባም። በክፉው ግዛት በተያዘ ዓለም (1 ዮሐንስ 5፡19) ውስጥ ካለ ባህል በእርግጥ ምን የተሸለ ነገር ልንጠብቅ እንችላለን?

ወደዚህ ያመዘነ አሉታዊ ተስፋ ማስቆረጥ ውስጥ ቤተክርስቲያን ስትወድቅ ስናይም ሊገርመን አይገባም። በውስጣችን የቀረው ኃጢያት ወደዚህ ያዘነበለ ነው እንዲሁም ክርስቲያኖች ከክፉው ኃይል ቋሚ ውጊያ አለባቸው (ኤፌሶን 6፡12)። በመንፈሳዊ ሕይወት ጸንቶ ለመቆም ጥብቅ የሆነ ነገሮችን መለየት ያስፈልጋል። 

ነገር ግን በውጊያው ቀውስ መሀል እርስ በእርስ ቤተኛ በሆኑ እሳቶች ልንጎዳዳ እና ማጽናናት ለመንፈሳዊ ሕይወት መጽናት አስፈላጊ እንደሆነ ልንረሳ እንችላለን።

ማጽናናት መንፈሳዊ ውጊያ ነው

ማጽናናት መንፈሳዊ ውጊያ ነው:: አንድን ሰው የምናጽናና ከሆነ ሰይጣንን እና የእራሳችንን ኃጢያት መፋለም ይጠይቀናል። 

ሰይጣን ሁል ጊዜ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይጥራል። “ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ” ነው (ራዕይ 12፡10)። አሽከሮቹም የሚንበለበሉ የክስ፣ የቅንአት እና መራርነት ፍላጻዎች ዘወትር ወደ እኛ ይወረውራሉ። (ኤፌሶን 6፡16) "ስለዚህ ጸንታችሁ ተቃወሙት።" (1 ጴጥሮስ 5፡9)

ኃጢያተኛ ማንነታችን ሌሎችን ተስፋ ማስቆረጥ ይፈልጋል። ከምንም በላይ እራስን ከፍ ማድረግን ይፈልጋል። በቅንአትም በመነሳትም የሌሎች ድካም እና ኃጢያት ላይ ማተኮር ያስደስተዋል። ስለ ሌሎች የምናስበው እና የምንናገረው ደግሞም የምንሰማው እና የምንረዳው አሉታዊ እንዲሁም ስንገስጻቸው ያለ ፍቅር የሆነበት ምክንያት ትዕቢት ነው።

የመጽናናት አምላክ” ግን (ሮሜ 15፡5) እነዚህን ጠላቶች ልናሸንፍበት እንድንችል “የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል” (ኤፌሶን 6፡17) የሆነ የጦር እቃ ሰጥቶናል። “በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና” (ሮሜ 15፡4) ተስፋ በሚኖረንም ጊዜ ደግሞ ጽናት ይኖረናል።

እንደ ባርናባስ የመሆን ጥሪ

ዮሴፍ በርናባስ የተባለው በነገሮች ሁሉ ውስጥ የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚያዩ ዓይኖች ስላሉት መሆን አለበት። ምንም አይነት ሥነ-መለኮታዊ ንትርክ ቢኖር ወይንም ስደት ወይንም የገንዘብ ችግር ወይንም ውድቀት ቢኖር በእግዚአብሔር ላይ ጠንካራ ተስፋ ነበረው። እንዳንድ ችግሮች ጓደኞቹን ተስፋ ሲያስቆርጧቸው በተደጋጋሚ የእግዚአብሔርን ተስፋዎች ተስፋ በሚሰጥ መልኩ እያስታወሳቸው ያጽናናቸዋል፤ያነቃቃቸዋል።

መሆንም የምንፈልገው እንዲሁ ነው። እንደ ባርናባስ ያሉ ሰዎች መሆን አለብን። እንደ ባርናባስ ያሉ ሰዎች የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እራሳቸውን የሚጨምሩ በውስጣቸውም ቃሉን የሚሰውሩ (መዝሙር 119፡11) ይህንን በማድረጋቸው በመንፈስ መመላለስ እና ማውራት የሚችሉ ናቸው (ገላትያ 5፡16)። ሲናገሩም “ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋቸው ከቶ አይወጣም” (ኤፌሶን 4፡29)።

ይሄ ጥሪ ነገሮችን አጥርተን ማሰብ አቁመን እርስ በእርስ እንደው በጎ ጥሩ እንሁን ማለት አይደለም። የመጽናናት ቁንጮው በርናባስ ሳይቀር ከጳውሎስ ጋር ስለማርቆስ ትንንቅ ገጥሟቸው ነበር (የሐዋርያት ሥራ 15፡36-39)። ይሁን እንጂ መገለጫው መጽናናት እንጂ ሂሳዊ ክርክር አልነበረም።

ስለዚህ ይህ ጥሪ ባለንበት ቦታ ሁሉ የማጽናናትን ልምድ እንድናሳድግ ነው። ጥሪው እንደ በርናባስ ማንነታችን እስኪሆን ድረስ በማጽናናታችን የምንገለጥ ልዩ ሰዎች እንድንሆን ነው። እንደ ባርናባስ ያሉ ሰዎች ለሰሚዎች ጸጋን ይሰጣሉ። ተስፋ ለቆረጡት በሰፊው ተስፋን ይጨምራሉ። 

እኔም እንደሚያስፈልገኝ እንደ በርናባስ አይነት ሰዎች እንድትሆኑ እርዳታ ካሻችሁ ሌሎችን ስለማበረታታት በጣም ጠቃሚ መጽሐፍ ሆኖ ያገኘሁትን ሳም ክራብትሪ የጻፈውን “Practicing Affirmation” የሚል መጽሐፍ እንድታነቡ እጋብዛችኋለሁ። ሳም እንደ በርናባስ ያለ እንደ በርናባስ ያሉ ሰዎችንም የሚያፈራ ሰው ነው።

ነገር ግን እንደ በርናባስ አይነት ሰው ለመሆን እና በእግዚአብሔር ወደ መጽናናት ልጆችነት የተለወጡ እና በመንፈስ የሚመራ መለየት ላቸው የምናገኛቸው ሰዎች ሁሉ ካገኘናቸው ጊዜ ይልቅ ተጽናንተው እንዲሄዱ ካስፈለገ እግዚአብሔርን በመጠየቅ መጀመር አለብን።

ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ” (1 ተሰሎንቄ 4፡18)

 

Originally Posted at DesiringGod.org, Translated by Joshua Terefe


 

Last modified on %AM, %17 %964 %2016 %01:%Dec
Jon Bloom

Jon Bloom serves as author, board chair, and co-founder of Desiring God. He is author of three books, Not by Sight, Things Not Seen, and Don’t Follow Your Heart. He and his wife live in the Twin Cities with their five children.

https://twitter.com/Bloom_Jon

የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ

ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል! ክፍል ሁለት - የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች እና መዘዞቹ በቀደመው ክፍል ላይ ‘ፖርኖግራፊ’ ሰዎችን ሱሰኛ የማድረግ ከ...

Ermias Kiros - avatar Ermias Kiros

ጨርሰው ያንብቡ

የእግዚአብሔር ልጆች ኃይል እና ልዩ መብት

ስለግል የፀሎት ጊዜያችሁ መለስ ብላችሁ የምታዩበት እና በመጪዎቹ ቀናት አንድ ወይንም ሁለት ነገሮችን ለማስተካከል የምታልሙበት ጊዜ አሁን ነው። በተለምዶ ለማደ...

David Mathis - avatar David Mathis

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.