Sunday, 19 May 2024

ልጓም የሌለው የምኞት ፈረስ

Posted On %PM, %10 %681 %2016 %18:%Dec Written by

አንድ ወንድ የሆነችን ልጅ ሰውነት ስለተመኘ ብቻ ሊያገባት ሲፈልግ፣ በዚች ምድር ላይ እንደእርሱ ያለ አፍቃሪ የሌለለ እስኪመስል ድረስ እራሱን “ሮማንቲክ” አድርጎ ያቀርብላታል።

ለአንድ ሴት ደግሞ እንደ “ሮማንቲክ” ወንድ የሚስብ ነገር የለም። በእርሷ ፍቅር ያበደ ይመስላታል። እውነታው ግን በተቃራኒው ፈጽሞ እንዳልወደዳት ነው። ጋብቻን ለመሰለ የረጅም ጊዜ ኃላፊነት ውስጥ ለመግባት ዝግጁ ነው? በፍጹም አይደለም። ለአንድ ምሽት  እንኳን ገላዋን ለማግኘት በጋብቻ ስርዓት ውስጥ ቢያልፍ ይገደዋል? በፍጹም! ምንም አይገደውም።

ሰውነቷን ስለሆነ እየተመኘ ያለው የማይታሰበውን እንኳን ለማድረግ ማበረታቻው ይህ ነው። አንዴ ለምኞት የተሰጠ ከሆነ፣ ሕይወቱን ሙሉ ምኞት በተባለ ሱስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ሲመራ ይኖራል።

የምኞት ችግር ይህ ሰው ከዚያች አንድ ምሽት በኋላ ከዚያች ቆንጆ ልጅ ጋር የነበረውን ነገር ስለሚጨርስ ነው። ያ ምሽት ከጋብቻቸው ቀን ቀጥሎ ያለው ቀን ላይ ያለ የጫጉላ ሽርሽር ቀናቸው እንኳን ቢሆን ለውጥ የለውም።

አዎን። ይህ ሲሆን ማየት በጣም ያሳዝናል። 

ከጫጉላ ሽርሽራቸው የመጀመሪያ ቀን በኋለ ከዚያች ቆንጆ ልጅ ጋር የነበረውን ነገር ይጨርሳል። ምኞት “ደህና ሁን” ብሎት ድንገት ለብቻው ትቶት ይሄዳል። ሹፌር ሆኖ መናገር እና ማድረግ ያለበትን ሲነግረው የነበረው ምኞት ስለነበር ያለ ምኞት ከዚች ልጅ ጋር እንዴት መኖር እንዳለበት አያውቅም።

ስለዚህ ከትዳሩ ውስጥ ቀስ ብሎ ይወጣል። አንዳንድ ጊዜ በእርግጥም ትቷት ይሄዳል፤ አሊያም በትዳሩ ውስጥ ቢቆይም እንኳን ከእርሷ ጋር ምንም ጉዳይ አይኖረውም። እንደዚህ ሲሆን ታዲያ አዲሲቷ ሙሽራ ከጋብቻቸው በፊት እንደነበረው ትኩረት አይሰጠኝም ወይንም አብሮኝ መሆን አይፈልግም እያለች ታጉረመርማለች።

የኔ ውድ ሰውየው ጨርሷል!

እዚህ ጋር ዋናው አስፈላጊ ጉዳይ ምኞት ከጋብቻ ጋር ብዙውን ጊዜ መቀላቀል አለመቻሉ ነው። ምኞትን እና ጋብቻን ለመቀላቀል መሞከር ዘይትን እና ውኃን ለመቀላቀል እንደመሞከር ነው። ጋብቻ እና ምኞት ልክ እንደ ውኃ እና ዘይት የየራሳቸውን ተፈጥሯዊ ይዘት እንደጠበቁ ተለያይተው ይኖራሉ።


ምኞትን እና ጋብቻን ለመቀላቀል መሞከር ዘይትን እና ውኃን ለመቀላቀል እንደመሞከር ነው። ጋብቻ እና ምኞት ልክ እንደ ውኃ እና ዘይት የየራሳቸውን ተፈጥሯዊ ይዘት እንደጠበቁ ተለያይተው ይኖራሉ።


ስለዚህ አንዲት ሴት ሰውነቷን ብቻ ሲመኝ የነበረን ሰው ስታገባ በሚያሳዝን ሁኔታ ወዲያው ከሠርጓ በኋላ ሕይወትን ለብቻዋ ልትጋፈጥ ትችላለች። ምንአልባትም ደግሞ ጸንሳ ወይም ትንንሽ ልጆችን ይዛ። አሊያም ሙሉ በሙሉ በሞተ ትዳር ውስጥ ትኖራለች። ለምን? ምክንያቱም አንዳንድ ወንዶች ምኞት የሕይወታቸውን ሞተር ካላንቀሳቀሰው ሊኖሩ ስለማይችሉ ነው። ስለዚህ ከትዳራቸው ውስጥ ይወጣሉ ወይም እንደ ባል እና አባት ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ይጎድላሉ።

በጣም የሚያሳዝን ክስተት ነው! የወሲባዊ (Pornnographic) ፊልሞች “ምኞት ከሕይወት ይልቅ አስፈላጊ ነው” የሚለው መልዕክት እያየለ ባለበት ባሁኑ ጊዜ ይህ ታሪክ በጣም የተለመደ እየሆነ እየመጣ ነው።

አንዳንድ ያላገቡ ክርስቲያን ወንዶች ሰውነቷን እንዲመኙ በማድረግ ታላቅ ደስታን ልትሰጣቸው የምትችል ሴትን ይፈልጋሉ። ይህችን ሴት ሲያገኟት ታዲያ ሰውነቷን ለማግኘት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። እንድታገባቸው ሊጠይቋት ይችላሉ። ብዙ ጊዜ ግን ችግሩ ከመጀመሪያው ምሽት በኋላ ይህችን ሴት አለመፈለጋቸው ነው።

ይሄ ለሴቲቱ በጣም ልብ የሚሰብር ነገር ነው! ምን ያህል ቆንጆ ደናግል ክርስቲያን ሴቶች ሰውነታቸውን ብቻ ሲመኝ የነበረ ወንድ አግብተው ከመጀመሪያዋ ምሽት በኋላ እንደ ቆሻሻ እየተቆጠሩ እንዳሉ ታውቃላችሁ? አዎን፤ ለመቁጠር እንኳን የሚያዳግቱ ሴቶች!

ታዲያ አንዲት ያላገባች ሴት እንዴት ነው በምኞት ካበደ ወንድ የፍቅር እንክብካቤ የመታወር ወጥመድ ልታመልጥ የምትችለው?

አጭር መልስ! እንደ እግዚአብሔር ልብ የሆነች ሴት በመሆን!

እንደ እግዚአብሔር ልብ የሆነች ሴት ሰውነቷን በሚመኝ ወንድ የፍቅር እንክብካቤ አትታለልም።

እንደ እግዚአብሔር ልብ የሆነች ሴት ምንም ትልቅ ቢሆን ትንሽ ውሳኔዋን አታምንም። ከአንድ ሰው ጋር ወደ ጓደኝነት መግባት ከፈለገች ጓደኝነት ከመጀመሯ በፊት የሌሎችን ሰዎች ምክር ትጠይቃለች። ሰውየው ማን እንደሆነ ከሌሎች ሰዎች ትጠይቃለች። ከሌሎች ሰዎች ጋር ጤነኛ ግንኙነት እንዳለው በእውነትም ለቃሉ ታማኝ የሆነ ሰው እንደሆነ ለማየት ከእራሱ ጋር፣ ከጓደኞቹ እና ከቤተሰቦቹ ጋር ጊዜ ታሳልፋለች። ምንም ዓይነት ግራ መጋባት እንዳይፈጠርበት በንጽሕና ለመኖር ያላትን መርሆች ትነግረዋለች። ከጋብቻ በፊት አብሮ መተኛትን “እንቢ” እያለች መልሳ ደግሞ በሚገናኙበት ጊዜ ገላዋን የሚያሳይ ልብስ እየለበሰች በመምጣት ሁለት ዓይነት መርሆችን በመያዝ ግራ አታጋባውም። በፍጹም እንዲህ አታደርግም። 

እንደ እግዚአብሔር ልብ ያልሆነች ለምኞትም የምትጋለጥ ሴት ዋነኛው መገለጫ የጸሎት እና ከእግዚአብሔር ቃል ጋር በግሏ ሕብረት የምታደርግበት ጊዜ አለመኖሩ ነው። አካሉ ለሆነችው ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እንግዳ ነች።  እግዚአብሔርን የመምሰል፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና የንጽሕና መርህ ካላቸው ሌሎች አማኞች ጋር በጣም ጥቂት የሚባል ሕብረት አሊያም ምንም ሕብረት የላትም። በሕይወቷ ውስጥ የሚገጥሟትንም ነገሮች በእራሷ ነው የምትወጣቸው። ከእግዚአብሔር እና ከህዝቡ በራቀች ቁጥር “ሔዋንን” (በውስጧ ያለውን የተረገመ ተፈጥሮ) የመሆን ተፈጥሯዊ ማጋደሏ ያይልና ይቆጣጠራታል። በሰው እና በእግዚአብሔር ላይ መደገፏን ታቆማለች። ከፈለገችው ትወስደዋለች። መልካም መስሎ ከተሰማት ትወስደዋለች። የሚያምር ከመሰለ ትወስደዋለች። አንድ ወንድ በምኞት ሰክሮ በሰውነቷ ሲጎመጅ ብታይ፤ ሀሳቡ ምን እንደሆነ ሳትጠይቅ የሚያቀርብላትን እንክብካቤዎች ሁሉ እንደ ሀሺሽ ትጋታቸዋለች። ከእርሱ ምንም አትጠይቅም። በትክክለኛው መንገድ እየሄደች እንደሆነ ሰዎችን ትጠይቃለች? ፈጽሞ ማንንም አትጠይቅም! ሰዎች ላይ የማትደገፍ ሰው ነች። ማለትም “የተማሩ አና ዘመናዊ ምዕራባዊያን” ክርስቲያን ነች! 

እዚህ ጋር በጣም የሚገርመው ነገር ሰውነቷን እየተመኘ ያለው ሰው ሳይቀር መሠረቷን ይዛ ከእርሱ ንጽሕናን እንድትጠብቅበት በውስጡ ይመኛል። ሰውነቷን ለመመኘት ሳይሆን እንደ ሰው ሊወዳት ይችል ዘንድ ሥጋዊ ተፈጥሮውን ሳይሆን ልቡን እና ነፍሱን ለመሳብ የምትችለውን ሁሉ እንድታደርግ ይፈልጋል።

ስለዚህ ይህንን እያነበባችሁ ያላችሁ ገና ያላገባችሁ ቆንጆ ክርስቲያን ሴቶች እባካችሁ ስሙኝ። ይገባኛል ዛሬ ላይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ንጽሕናቸውን እየጠበቁ ያይደሉ ሴቶች ሁሉ እያገቡ እያያችሁ እናንተ ብቻችሁን ስትቀሩ የእግዚአብሔርን ፍቃድ መጠየቅ ከባድ እንደሆነ።

የኔ ውድ አይጭነቅሽ። ምን ያህል ያገቡ ሴቶች ከትዳራቸው ለመውጣት መንገድ እየፈለጉ እንደሆነ ሀሳቡ የላችሁም። የኔ ውድ፤ ጭንቀትሽን ሁሉ በክርስቶስ ላይ እያሳረፍሽ ጸንተሸ ጠብቂ።

ወዳጄ ሆይ ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ልብ የሆነች ሴት ለመሆን ወስኚ። ብዙ ክርስቲያን ሴቶችን እያጠመደ ያለ በሚመስለው በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትውደቂ። በዙሪያሽ ያሉ ሴቶች ሲያገቡ ስታዪ አትደንግጪ። አግብቶ በንጋታው እንደ ቆሻሻ ከመጣል ይልቅ ሕይወታችሁን ሙሉ ሳታገቡ ብትኖሩ ይሻላችኋል። አንቺ የተወደድሽ፤ እግዚአብሔርን ፈልጊ! እርሱን እና መንገዱን ብቻ ፈልጊ ከመልካም ነገርም ሁሉ አትጎዪም (መዝሙር 34፡10)።

አንቺ የተወደድሽ፤ እግዚአብሔር የሚያስፈልግሽን ያውቃል። በአንቺ ውስጥ ያደረጋቸው እርሱ እራሱ እያንዳንዳቸውን ሊፈጽማቸው ነው። ከማግባትሽ በፊት እድሜሽ መሄዱ እንደሚያሳስብሽ ያውቃል። ሌሎች ጓደኞችሽ እያገቡ አንቺ ግን ሕይወትሽን ሙሉ ሳታገቢ ልትቀሪ መሆኑ እንደሚያሳስብሽ ያውቃል። ያውቃል! ትግልሽን በሙሉ ያውቃል። ስለዚህ እርሱ እንዲፈጽመው ይህንን ለእርሱ ትተሸ የእርሱ ብቻ ለመሆን ጥረትሽን አድርጊ። የቤተ ክርስቲያን አንድ አካል ሁኚ። ከሌሎች አማኞች ጋር ስስ የሆነ ግንኙነትሽን አቁሚ። እውነተኛ በመሆን እንዳንቺ ጓደኛ ለሚያስፈልጋት ጓደኛ ሁኚ።  

የሚያስፈልግሽን ሁሉ ክርስቶስ እንዲፈጽማቸው ትተሽ ሌሎችን ከፍ ለማድረግ ፈልጊ።

ኦ ሃሌሉያ! የዚያን ጊዜ ታማኙ አምላክሽ ስለአንቺ ሲሠራ ታያለሽ። በሚያስደንቀው ጉብኝቱ ያስደንቅሽ። ከዚያም በሕይወት ታሪክሽ ላይ “ከዚያም እግዚአብሔር                      አሰባት” (ስምሽን አስገቢበት) ተብሎ ይጻፋል።

ያንቺ አምላክ ታማኝ ነው! የእርሱ ብቻ በመሆን ታማኝነቱን ፈትኚው!

እርሱ ታማኝ ነው! የእርሱ ብቻ በመሆን ታማኝነቱን ፈትኚው!

 

Originally Posted at Appeal For Purity, Translated by Joshua Terefe

Last modified on %AM, %11 %270 %2016 %08:%Dec
Meskerem Kifetew

Dr. Meskerem Tadesse Kifetew is the founder and president of Appeal for Purity Ministry

Dr. Mesekrem completed her doctorate degree in pharmacy from the University of Maryland and graduated in 2007. She then worked as a licensed pharmacist in the state of Maryland for six years. On the seventh year, she accepted the call of God to give all her time and energy to spread the truth of God in the area of sexual purity and she established a ministry called Appeal for Purity in 2013. 

Dr. Meskerem is now a full time minister of the Appeal for Purity Ministry, spending most of her time writing different articles in the area of sexual purity on social media such as Facebook and Twitter.  She also speaks at different churches traveling to different countries and doing counseling in different areas; marriage, sexual addiction and life coaching. 

Her first book, Beyond the Fairy Tale, was released throughout America, Europe and Australia in 2015 and within three months of its release, her book was ranked as first from its class on Amazon.com.

Dr. Meskerem, with her husband of 19 years and three of her teenage kids, resides in Maryland.

appealforpurity.org/

አሮጌው እኔ አዲስ ሲሆን

አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ። የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእ...

Marshall Segal - avatar Marshall Segal

ጨርሰው ያንብቡ

እግዚአብሔር ህዝቡን የሚመራባቸው አራት መንገዶች

እግዚአብሔር ህዝቡን በፍቃዱ ውስጥ ሊመራባቸው የሚችላቸው ቢያንስ አራት መንገዶች ይታዩኛል።

John Piper - avatar John Piper

ጨርሰው ያንብቡ

 

The views and opinions expressed on Daily Injera are solely those of the original authors and our contributors. These views and opinions do not necessarily represent Daily Injera or our Staff.

Newsletter

Subscribe to our newsletter. Don’t miss any article, devotionals or wallpapers.

We do not spam!

You're automatically subscribed to bi-weekly articles and daily devotionals. You can customize your subscription settings here.